የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ምልክቶቻቸውን ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድ እያስገቡ መሆኑን አስታወቁ፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጥር 12 ቀን 2013 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ እንዳመላከተው ስድስተኛው አገር አቀገፍ ምርጫ ለማከናወን ይፋ ባደረገው ሰሌዳ ላይ ፓርቲዎች የምርጫ ምልክቶቻቸውን ለቦርዱ እንዲያስገቡ ማሳሰቡ ይታወሳል፡፡በወጣው የጊዜ ሰሌዳ ላይ ከተጠቀሱት ተግባራት መካከል አንዱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ምልክት መረጣ ሲሆን በጊዜ ሰሌዳው ላይ ከጥር 13-24 ድረስ የምርጫ ምልክት ማስገቢያ እና መወሰኛ ጊዜ እንደሆነ ተቀምጧል።

በዚህም የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች ምልክቶቻቸውን ለቦርዱ እያስገቡ መሆኑን ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትሕ ፓርቲ(ኢዜማ) የህዝብ ግንኙነት ሐላፊ አቶ ናትናኤል ፈለቀ ቦርዱ የጠየቀውን ምልክት በትናንትናው ዕለት ማስገባታቸውን ለአሐዱ ገልፀዋል፡፡የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት(መኢአድ) ሊቀመንበር አቶ ማሙሸት አማረ የምርጫ ምልክታቸውን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ገቢ ስለማድረጋቸው ተናግረዋል፡፡የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) የህዝብ ግንኙነት ሐላፊ አቶ ጣሂር መሃመድ ምርጫ ቦርድ የጠየቀውን የምርጫ ምልክት ለማስገባት ዝግጅት ማጠናቀቃቸውን ለአሐዱ አረጋግጠዋል፡፡

***********************************************************************

ቀን 14/05/2013

አሐዱ ራዲዮ 94.3

The post የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ምልክቶቻቸውን ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድ እያስገቡ መሆኑን አስታወቁ፡፡ appeared first on አሐዱ ቲቪ እና ራድዮ 94.3.

Source: Link to the Post

Leave a Reply