የቱሪዝም ሚኒስትር ለሹፌሮች ፕሮቶኮል በሚል ከ50ሺህ ብር በላይ ወጪ ማውጣቱ ተነገረ። ሚኒስቴር መስራቤቱ ለፕሮቶኮል በሚል ለሶስት ሹፌሮች ለእያንዳንዳቸው ከ50ሺህ ብር በላይ ወጪ በማድረግ…

የቱሪዝም ሚኒስትር ለሹፌሮች ፕሮቶኮል በሚል ከ50ሺህ ብር በላይ ወጪ ማውጣቱ ተነገረ።

ሚኒስቴር መስራቤቱ ለፕሮቶኮል በሚል ለሶስት ሹፌሮች ለእያንዳንዳቸው ከ50ሺህ ብር በላይ ወጪ በማድረግ ሙሉ ልብስ መግዛቱን የተወካዮች ምክር ቤትን አነጋግሯል፡፡

የቱሪዝም ሚኒስትር በተጋነነ ሁኔታ ለሹፌሮች ሙሉ ልብስ ማሰፋቱ ተገቢ አይደለም ብሏል የተወካዮች ምክር ቤት ።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የቱሪዝም ሚኒስትር በተለያዩ ዘርፎች የተጋነነ ወጪ ማውጣቱን ባደረገው ግምገማ ገልጿል።

ቋሚ ኮሚቴው የሚኒስቴር መስራቤቱ የኦዲት ግኝት በገመገመበት ወቅት በተለያዩ ዘርፎች የኦዲት ግኝት ማግኘቱን አስታውቋል።

የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ ወ/ሮ አራሪ ሞሲሳ እንደተናገሩት በማን አለብኘነት ስሜት የሀገር እና የመንግስት ሃብት እየባከነ ነው ብለዋል።

በዚህም ቋሚ ኮሚቴው ወጪው የተጋነነ መሆኑን ገምግሞ ሚኒስቴር መስራቤቱ በፋይናንስ ዘርፉ ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ ወስዶ ለታህሳስ 25 ቀን 2016 አመት ለቋሚ ኮሚቴው እንዲያቀርብ ተጠይቋል።

ሄኖክ ወ/ገብርኤል

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ታህሳስ 17 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Telegram (https://t.me/ethiofm107dot8

Source: Link to the Post

Leave a Reply