“የቱ ጋር ነህ” የድምጻዊ ዲበኩሉ ታፈሰ አዲስ አልበም!”የቱ ጋር ነህ “የተሰኘው የድምፃዊ ዲበኩሉ ታፈሰ የመጀመሪያው አልበም ታህሳስ 28 ቀን 2015 ዓም ለአድማጭ ሊያደርስ መሆኑ…

“የቱ ጋር ነህ” የድምጻዊ ዲበኩሉ ታፈሰ አዲስ አልበም!

“የቱ ጋር ነህ “የተሰኘው የድምፃዊ ዲበኩሉ ታፈሰ የመጀመሪያው አልበም ታህሳስ 28 ቀን 2015 ዓም ለአድማጭ ሊያደርስ መሆኑ ተገልጿል።

ከዚህ ቀደም በጃኖ ባንድ የሚታወቀው አርቲስቱ አልበሙን ከኬኔቲክ ዳውን ጋር በመሆን መስራቱን የተናገረ ሲሆን ፤ ትላልቅ የሙዚቃ ባለሞያዎች በግጥም እና በዜማ ተሳትፈዋል ብሏል።

ከባለሞያዎቹም መካከል ይልማ ገብረአብ ፣ ልጅ ማይክ እንዲሁም አርቲስቱም በግጥም መሳተፉን ተናግሯል።

አልበሙ 13 የሙዚቃ ስራዎች የተካተቱበት ሲሆን በቅርቡ አንድ ቪዲዮ ለአድማጭ መድረሱን ተጠቁሟል።

የአልበሙ ስያሜ ሰዎች ያሉበትን እና የነበሩበትን እንዲመለከቱ በማሰብ “የቱ ጋር ነህ?” ሲል መጠሪያ እንደተሰጠው ድምጻዊው ተናግሯል።

በእሌኒ ግዛቸው
ታህሳስ 21 ቀን 2015 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
Twitter https://twitter.com/EthioFM
YouTube https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast
Website https://ethiofm107.com/
ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።

Source: Link to the Post

Leave a Reply