የታለመለት የነዳጅ ድጎማ ከ160 ሺ በላይ ተሸከርካሪዎች ላይ ተግባራዊ መሆን ጀመረ

ዕረቡ ሰኔ 29 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሸከርካሪዎችን ብቻ ተጠቃሚ የሚያደርገው የታለመለት የነዳጅ ድጎማ ከዛሬ ሰኔ 29 ቀን 2014 ጀምሮ ተግባራዊ መሆን መጀመሩን የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር አስታወቀ።

በመላ አገሪቱ የሚገኙ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሸከርካሪዎች የታለመለት የነዳጅ ድጎማ ተጠቃሚ ለመሆን አስፈላጊ መረጃዎችን በመስጠት በኢትዮ ቴሌኮም የሽያጭ ማዕከላት በኩል ምዝገባ ማድረጋቸው የሚታወስ ነው፡፡

የብሔራዊ የታለመለት የነዳጅ ድጎማን በቴክኖሎጂ ለመደገፍ በኢትዮ ቴሌኮም በኩል መተግበሪያ በልፅጎ አስተማማኝና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡

በዚህም መሠረት በቴሌ ብር በኩል አገልግሎቱን ለማግኘት የተመዘገቡ ከ160 ሺ በላይ ተሸከርካሪዎች ከዛሬ ጀምሮ መተግበሪያውን በመጠቀም ይስተናገዳሉ፡፡

የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎች ዓመታዊ የነዳጅ ፍጆታ ተቀራራቢ የሊትር መጠን ግምት በጥናት መለየቱና እያንዳንዱ ተሸከርካሪ የሚጠቀመውን የነዳጅ መጠን ያገናዘበ ስሌት በመቀመጡ ተሽከርካሪዎቹ ያለ ብክነት የታለመ የነዳጅ ድጎማን ጥቅም ላይ እንዲያውሉ የሚያግዝ ነው ተብሏል፡፡

የታለመለት የነዳጅ ድጎማ ተጠቃሚ የሆኑ የህዝብ ትራንስፖርት ተሸከርካሪዎች ብቻ ከላይ በቀረበው ምስል ላይ በተገለፀው ዝርዝር መሠረት  ዕለታዊ የነዳጅ መጠን  ማግኘት ይችላሉ፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply