የታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ 2ኛው ተርባይን የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ጀመረ

ሐሙስ ነሐሴ 5 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በዛሬው ዕለት የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በኹለተኛ ተርባይን የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ጀምሯል።

ጠቅላይ ሚኒስትር (ዶ/ር) ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች በቤንሻንጉል ጉሙዝ ጉባ ወረዳ በታደሙበት ዝግጅት ላይ ነው ኹለተኛው ተርባይን ኃይል ማመንጨት የጀመረው።

የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ካሉት 13 ተርባይኖች መካከል ዩኒት 9 የሚባለው ኹለተኛው ተርባይን የተሳካ ተከላ እና ሙከራ ከተደረገ በኋላ ኃይል የማመንጨት ሥራው እውን ሆኗል።

ዛሬ በይፋ ሥራ የጀመረው ኹለተኛው ዩኒት 375 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም እንዳለው ተገልጿል።

ባለፈው የካቲት ወር ላይ 270 ሜጋ ዋት የሚያመነጨው ዩኒት10 ኃይል ማመንጨት መጀመሩ ይታወሳል።

ይህን ተከትሎም ታላቁ የኢትዮጵ ህዳሴ ግድብ የዛሬውን ጨምሮ በአጠቃላይ 540 ሜጋዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ያመነጫል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply