የታላቁ የኢትዮጵያ  ህዳሴ  ግድብ በሚገነባበት ጉባ ወረዳ   17 ሰዎች በታጣቂዎች ተገድለዋል፡፡  አሻራ (ታህሳስ17፣ 2013ዓ.ም)  ታህሳስ 15  ቀን በጉባ ወረዳ አይሲድ ቀበሌ የተደራጁ…

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በሚገነባበት ጉባ ወረዳ 17 ሰዎች በታጣቂዎች ተገድለዋል፡፡ አሻራ (ታህሳስ17፣ 2013ዓ.ም) ታህሳስ 15 ቀን በጉባ ወረዳ አይሲድ ቀበሌ የተደራጁ…

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በሚገነባበት ጉባ ወረዳ 17 ሰዎች በታጣቂዎች ተገድለዋል፡፡ አሻራ (ታህሳስ17፣ 2013ዓ.ም) ታህሳስ 15 ቀን በጉባ ወረዳ አይሲድ ቀበሌ የተደራጁ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት 17 ሰዎች እንደተገደሉ የጓንጓ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ገልፃል፡፡ 11ዱ ዛሬ በመከላከያ የተቀበሩ ሲሆን፣ 6ቱን ታጣቂዎች ነዳጅ አርከፍክፈው አቃጥለዋቸዋል፡፡ ታጣቂዎቹ መተከል ላይ ባሉ አመራሮች ጉያ ስር እና በሱዳን ብሉ ናይል ግዛት ትጥቅ እና ስንቅ እንደሚቀርብላቸው ተረጋግጧል፡፡ የመተከል አመራሮች ደግሞ ንፁሃን እንዲገድሉ ፌዴራል ባሉ በብልፅግና አመራሮች እንደሚደገፉ ተገምቷል፡፡ ዛሬ የመተከል ዞን ባወጣው መግለጫ እንደገለፀው በማህበራዊ ሚዲያ የሚናፈሰው ሁሉ ስህተት ነው ሲሉ በሟቾች እና በተፈናቀሉት ላይ አላግጠዋል፡፡ ከ100 ሺ በላይ ንፅሃን ሲፈናቀሉ እና ከአንድ ሺ በላይ እስካሁን በግፍ ሲታረዱ የክልሉ አመራር ምንም አይነት የመቆርቆር ስሜት አላሰየኝም፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ሀይል ተጨምሮ ወደ መተከል ገብቷል ያሉት ፈፅሞ ስህተት እንደሆነ አሻራ በተደጋጋሚ አሳውቋል፡፡ መከላከያው በፖለቲካው ብልሽት ምክንያት እርምጃ መውሰድ ሲሳነው ተስተውሏል፡፡ የአማራ ልዮ ሀይል ገብቶ ንፅሃንሰ እንዳይታደግ ማዕከላዊ መንግስቱ ከልክሏል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply