የታሰሩት የባልደራሶቹ ሰናይት ታደገና ሱራፌል አንዳርጌ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮምሽን(3ኛ) ገብተዋል! ባህርዳር:- ሚያዚያ 27/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ # የእስሩ ዘ…

የታሰሩት የባልደራሶቹ ሰናይት ታደገና ሱራፌል አንዳርጌ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮምሽን(3ኛ) ገብተዋል! ባህርዳር:- ሚያዚያ 27/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ # የእስሩ ዘመቻ ቀጥሏል፣ በእስሩ ዘመቻ ዙሪያ ከቀኑ 10:30 ሰዓት በዋሽንግተን ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል! / የኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች የጣሊያን ወራሪ ኃይልን ድል የአደረጉበትን 81ኛ ዓመት የድል መታሰቢያ ቀን ለማክበር እንቅስቃሴ ያደረጉት የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) አባሏ ወ/ሮ ሰናይት ታደገ እና የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ክፍል የካሜራ ባለሙያው አቶ ሱራፌል አንዳርጌ ታስረው ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፤ 3ኛ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደዋል። የወሰዱትን የአበባ ጉንጉን በድል ሐውልቱ ስር እንዳያስቀምጡ ተከልክለው ነበር ለእስር የተዳረጉት። ለቀረፃ ይዘውት የወጡትን የቪዲዮ ካሜራ ጨምሮ ንብረቶቻቸውም በፖሊስ ተይዘዋል። ከሁለቱ በተጨማሪ ሰሞኑን በአዲስ አበባ ለእስር ከተዳረጉት መካከል የባልደራሱ ቢኒያም ታደሰ፣ ታዋቂው ጋዜጠኛ ጎበዜና ሌሎች በርካታ የዐማራ ክልል ወጣቶች ይገኙበታል። ይህን የእስር ዘመቻ አስመልክቶ በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የኢትዮጰያ ኤምባሲ ፊት ለፊት ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል። በዚህ ባልደራስ የፌስቡክ ገፅ እና በሌሎች ሚዲያዎች ከቀኑ 10:30 ጀምሮ በቀጥታ (live facebook) ይተላለፋል። ይከታተሉት። ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- ቴሌግራም :- https://t.me/asharamedia24 Facebook :- https://www.facebook.com/asharamedia24 youtube :- https://www.youtube.com/channel/UChir2nIy58hlLQRYyHIQeHA Telegram (https://t.me/asharamedia24) Ashara Media – አሻራ ሚዲያ ስልክ፥ +251984000629 ዩትዩብ፥ https://bit.ly/33XmKro

Source: Link to the Post

Leave a Reply