የታሸገ ውሃ ላይ ምክንያቱ ያልተገለጸ ከፍተኛ የዋጋ ጨማሪ እየተስተዋለ ነው።

የውሃ አከፋፋዮች ወትሮ ይሸጡበት ከነበረው ዋጋ ጨምረው እየሸጡ ይገኛሉ።

በሱቆች 25 ብር ይሸጥ የነበረው 2ሊትር ውሃ አሁን 30 ብር እየተሸጠ ይገኛል።

ከዚህ በፊት ሱቆች ከአከፋፋዮች 20ብር ይረከቡ የነበረ ሲሆን አሁን ግን በ25 ብር እየተረከቡ እንዳሉ ነግረውናል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም ይህንን ጉዳይ ለማረጋገጥ በየሱቆች ቅኝት አድርጎ እውነት መሆኑን አረጋግጧል።

በየሱቆች እየተዟዟሩ ውሀ የሚያከፋፍሉ ነጋዴዎች ለዋጋው ጭማሪ ግልጽ የሆነ ምክንያት እንደሌለ ተናግረዋል።

አከፋፋዮች እንደተናገሩት ከሆነ ፋብሪካዎች እኛም ላይ ጭማሪ አድርገውብናል ብለዋል።

ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ኢትዮ ኤፍ ኤም የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴርን የጠየቀ ሲሆን እስካሁን መረጃው እንደሌለው ገልጾ በቀጣይ መረጃዎችን አሰባስቤ ማብራሪያ እሰጥበታለሁ ብሎናል፡፡

በሄኖክ ወ/ገብርኤል

ጥቅምት 09 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply