የታንዛኒያ የገንዘብ ሚኒስትር በራሳቸውም በመንግስታቸውም ላይ ቁጣን ቀስቅሰዋል፡፡

የሀገሪቷ ፕሬዝዳንት ጆን ማጉፉሊ በሀገራቸው የኮቪድ-19 ስርጭት ጉዳይ ዙሪያ የተለሳለሰ አቋም ነበራቸው፡፡ልክ እንድ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዓይነት በሽታውን ከመጤፍም ያለመቁጠር ባህሪ ነበራቸው፡፡ሆኖም ከጥቂት ቀናት በፊት ፕሬዝዳንት ማጉፉሊ በሽታው በሀገራቸው ከፍተኛ የስጋት ደረጃ ላይ እንደሚገኝ አስታውቀው ነበር፡፡

ትላንትናም የሀገሪቱ የገንዝብ ሚኒስትሩ ፊሊፕ ምፓንጎ ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት ወደ መድረክ ሲወጡ ክፉኛ እያሳላቸውና ትንፋሽ እያጠራቸው ነበር የታዩት፡፡ይህም በተንቀሳቃሽ ምስል ተቀርፆ የተለቀቀው የዜና ሽፋን በሀገሪቷ ግርምትን ብቻ ሳይሆን ቁጣን ቀስቅሷል፡፡

ሰውዬው 10 ለሚሆኑ ጋዜጠኞች ነው በዚህ መልኩ መግለጫውን የሰጡት፡፡ በኮቪድ-19 ምክንያት ህይወታቸው አልፏል ተብሎ አሉባልታ የተነዛባቸው ሚኒስትሩ እኔ አልሞትኩም አለሁኝ ለማለት ነበር መግለጫ ለመስጠት ወደ መድረክ የወጡት፡፡የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል አለማድረጋቸውም አነጋጋሪ ከመሆን ባለፈ የሚያሳዩት የነበረው የህመሙ ምልክት ስጋትን ፈጥሯል፡፡ ምንጭ፡- አልጄዚራ ነው፡፡

ቀን 19/06/2013

አሐዱ ራድዮ 94.3

Source: Link to the Post

Leave a Reply