#የታይፎይድ በሽታ (Typhoid Fever)የታይፎይድ በሽታ ሳልሞኔላ ታይፊ በሚባል የባክቴሪያ ዓይነት የሚመጣ በሽታ ነው፡፡ እንደ ኢትዮጵያ በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት በስፋት የሚከሰት በ…

#የታይፎይድ በሽታ (Typhoid Fever)

የታይፎይድ በሽታ ሳልሞኔላ ታይፊ በሚባል የባክቴሪያ ዓይነት የሚመጣ በሽታ ነው፡፡

እንደ ኢትዮጵያ በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት በስፋት የሚከሰት በሽታ ነው።

#መተላለፊያ መንገዶቹ

በዋነኝነት ይህ በሽታ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈው በንጽሕና ጉድለት ነው። ለዓብነት:-
>ማንኛውም ሰው ምግብ ሲያዘጋጂም ሆነ ሲያቀርብ በውኃና በሳሙና እጆቹን ካልታጠበ፤
>ውሃን ሳይታከም(ሳይጣራ) ምግብ ለማብሰል ወይም ዕቃ ለማጠብ የምንጠቀምበት ከሆነ ፡፡

#የታይፎይድ በሽታ ምልክቶች ምን ምን ናቸው?

ተሕዋስያኑ ወደ ሰውነታችን በገቡ ከ 5 እስከ 21 ቀን ባለው ጊዜ ውስጥ ምልክቶችን ማየት እንጀምራለን። ምንም ዓይነት ሕክምና ካላገኘን በ 3 ክፍሎች የሚመደብ ምልክቶች ይኖሩናል።

በመጀመሪያ እየጨመረ የሚሄድ ትኩሳት ፤ብርድ ብርድ ማለትና የልብ ምት መቀነስ ነው።

ሁለተኛ ላይ የሆድ ቁርጠት፣ ድርቀት፣ተቅማጥ ፣ደረት እና ሆድ ቆዳ ላይ የሚወጣ “ሮዝ ስፖት” የሚባል ቀይ ሽፍታ ሊታይ ይችላል።

ሦስተኛው ላይ የጉበት እና ጣፊያ እብጠት፣ የአንጀት መድማት እና መበሳት በሽታው እየተባባሰ ሲሄድ ወደ ደም መመረዝ፣ራስን መሳት እና ሞት ሊያስከትል ይችላል።

#የታይፎይድ በሽታ ምርምራዎች ምን ምን ናቸው?

ካልቸር (culture) – ይህ ምርመራ ከደም፣ ከሰገራ ወይም ከሽንት በሚወሰድ ናሙና ይሠራል፡፡

ዋይዳል (widal) – ይህ ምርመራ ሰውነታችን የታይፎይድ በሽታን ለመከላከል የሚያመነጫቸው አንቲቦዲ የሚባሉ ንጥረ ነገሮችን የሚመረምር ነው፡፡በሀገራችን ውስጥ በብዛት የምንጠቀምበት ምርመራ ነው።

#የታይፎይድ በሽታን እንዴት ማከም ይቻላል?

ታይፎይድ ተገቢውን ህክምና ካገኘ በቀላሉ የሚድን በሽታ ነው።

በሐኪሙ ትእዛዝ መሠረት እስከ 2 ሳምንታት ድረስ የሚቆይ የፀረ ባክቴሪያ (አንቲባዮቲክ) መድኃኒቶችን መውሰድ፡፡

#የታይፎይድ በሽታን መከላከል ይቻላል?

ምግብ ከመሥራት (ከማዘጋጀት) ወይም ከመመገብ በፊት እጅን በሳሙና እና በውሃ መታጠብ፡፡

በሚገባ የበሰለ እና ትኩስ የሆነ ምግብ መመገብ፡፡

አትክልቶችን ወይም ፍራፍሬዎችን በሚገባ ካጠቡ በኋላ መመገብ፡፡

የታሸገ ውሃ ወይም ፈልቶ የቀዘቀዘ (የታከመ) ውሃ መጠቀም፡፡

በልዑል ወልዴ

ጥር 21 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Source: Link to the Post

Leave a Reply