የታዳሽ አረንጓዴ ልማት በኢትዮጵያ በሚል ርዕስ በሮም የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስተባባሪነት ዓለም አቀፍ ዌቢናር ተካሄደ

የታዳሽ አረንጓዴ ልማት በኢትዮጵያ በሚል ርዕስ በሮም የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስተባባሪነት ዓለም አቀፍ ዌቢናር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የታዳሽ አረንጓዴ ልማት በኢትዮጵያ በሚል ርዕስ በሮም የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በትብብር ያዘጋጀው ዌቢናር ተካሄደ።

“የታዳሽ አረንጓዴ ልማት በኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ የተካሄደውን ዌቢናሩን በጣሊያን የተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት የኢንቨስትመንት እና ቴክኖሎጂ ፕሮሞሽን፣ በጣሊያን መንግስት እና በሮም የኢትዮጵያ ኤምባሲ በትብብር ያዘጋጁት ነው።

በዌቢናሩ ላይ በጣሊያን የተመድ የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት የኢንቨስትመንት እና ቴክኖሎጂ ፕሮሞሽን፣ በኢትዮጵያ የተመድ የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት፣ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን፣ ከውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ የገጠር ኢነርጂ ልማት እና ፕሮሞሽን ማዕከል፣ ከኢትዮጵያ የንግድና የዘርፋ ማህበራት ምክር ቤት፣ ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም ሌሎችም ኃላፊዎች ተገኝተው ገለፃ አድርገዋል።

በጣሊያን የኢትዮጵያ አምባሳደር ዘነቡ ታደሰ በኢትዮጵያ የተካሄደውን የኢኮኖሚ ሪፎርም፣ በዘርፉ የተደረጉ የፖሊሲ እና ህጋዊ ማዕቀፎች ማሻሻያ፣ ስለ አረንጓዴ እና ታዳሽ የሃይል ምንጮች፣ ለባለሃብቶች ስለሚደረጉ ማበረታቻዎች እና ልዩ ትኩረት የሚሰጣቸውን ዘርፎች በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በተጨማሪም የተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት የኢንቨስትመንት እና ቴክኖሎጂ ፕሮሞሽን በጣሊያን በኢትዮጵያ ለአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ለሚያደርገው ድጋፍ ምስጋና ማቅረባቸውን በሮም የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያወጣው መረጃ ያመለክታል።

The post የታዳሽ አረንጓዴ ልማት በኢትዮጵያ በሚል ርዕስ በሮም የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስተባባሪነት ዓለም አቀፍ ዌቢናር ተካሄደ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply