“የታገቱ የአማራ ሴት ተማሪዎች ቤተሰብ እምባ አልታበሰም፤ ባለ ስልጣናቱ ግን ወንበርና መኪና እየቀያየሩ በምቾት አሉ” ስትል ጋዜጠኛ ማዕዛ መሐመድ ተናገረች። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ   ታ…

“የታገቱ የአማራ ሴት ተማሪዎች ቤተሰብ እምባ አልታበሰም፤ ባለ ስልጣናቱ ግን ወንበርና መኪና እየቀያየሩ በምቾት አሉ” ስትል ጋዜጠኛ ማዕዛ መሐመድ ተናገረች። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታ…

“የታገቱ የአማራ ሴት ተማሪዎች ቤተሰብ እምባ አልታበሰም፤ ባለ ስልጣናቱ ግን ወንበርና መኪና እየቀያየሩ በምቾት አሉ” ስትል ጋዜጠኛ ማዕዛ መሐመድ ተናገረች። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታህሳስ 14 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በህዳር 24 ቀን 2012 ዓ.ም በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርስቲ በፅንፈኞች ከሚፈፀምባቸው ጥቃት ለመሸሽ ሲሉ ከግቢ የወጡ 17 የሚሆኑ አብዛኞቹ በጾታ ሴቶች የሆኑ የአማራ ተማሪዎችን የበላ ጅብ እስካሁን አልጮኸም። ነገሩን በተደራጀ መንገድ አጣርቶ ስለታጋቾች እጣ ፈንታ ተጨባጭ መረጃ ሊነግር አለመቻሉ በብዙዎች ዘንድ እያስወቀሰው ነው፤ እንዲያውም በተለያዩ የመንግስት አካላት ሲሰጡ ከነበሩ እርስ በርስ የተጣረሱ መረጃዎች አኳያ እና የታጋች ቤተሰቦችን ለማፈን ሲደረግ ከነበረው ያልተገባ የማሰርና የማዋከብ እንቅስቃሴ ተነስተው ይህ የሚያሳየው መንግስት የሴራው ተባባሪ ነው የሚሉም በርካቶች ናቸው። ትናንት ታህሳስ 13 ቀን 2013 ዓ.ም አንደኛ ዓመት የታጋች ተማሪዎችን የመታሰቢያ ፕሮግራም ካዘጋጁት አንዷ የሆነችው ጋዜጠኛ ማዕዛ መሀመድ በታገቱ ተማሪዎች ጉዳይ ንግግር ስለማድረጓ ተገልጧል። ማዕዛ ስትቀጥል በታገቱ ተማሪዎች ጉዳይ ማድረግ ያለብንን እያደረግን ነው፤ በዚህም ከታገቱ 17 ተማሪዎች ውስጥ የ16ቱን ቤተሰቦች አግኝተን አናግረናል ነው ያለችው። ጋዜጠኛዋ የታገቱ የአማራ ተማሪዎችን አንደኛ ዓመት በማሰብ በተዘጋጀው መድረክ እንደተናገረችው ወሎ፣ ጎጃምና ጎንደር ባሉ የገጠር ቀበሌዎች ተዟዙረው መረጃ ሰብስበዋል። የታጋቾችን ፎቶም ከቤተሰቦቻቸው እና ከትምህርት ቤት ለቅመው ይዘዋል። የአንዷን ታጋች ተማሪ ቤተሰብ ግን ማግኘት አልቻልንም ያለችው ማዕዛ ምክንያቱም አለች ልጅቷ ገና የ12ኛ ክፍል ተማሪ በመሆኗ እና ቤተሰቦቿ የሚኖሩትም ወለጋ በመሆኑ ነው ስትልም አክላለች። ወለጋ መሄድ አልቻልንም። ወለጋ አካባቢ የሚኖር ተቆርቋሪ ሰው ካለ የልጅቷን ስም እንሰጠዋለን። ወላጆቿን በመጠየቅ መረጃ ሊሰጠን ይችላል ስትልም ተደምጣለች። ጋዜጠኛዋ “ይሄን የምናደርገው ቢያንስ ታሪክ እንዳይወቅሰን ነው። ህይወታቸውን ማትረፍ ባንችል እንኳን፣ ቢያንስ መረጃውን ለትውልድ ማስተላለፍ አለብን።” ስትል ተናግራለች። የታገቱ የአማራ ሴት ተማሪዎች ከታገቱ አንድ አመት ሞልቷቸዋል፣ የቤተሰቦቻቸው እምባ አልታበሰም፤ ባለ ስልጣናቱ ግን ወንበርና መኪና እየቀያየሩ በምቾት አሉ። ስትል ወቅሳለች። ምንጭ_ፈለገ ግዮን_ማዕዛ መሐመድ – በታገቱ ተማሪዎች አንደኛ አመት መታሰቢያ ላይ የተናገረችው ሲል በይፋዊ የትስስር ገጹ ካሰፈረው

Source: Link to the Post

Leave a Reply