‹‹የትህነግ የጦር አበጋዞች መንግሥትን ነቅለን፣ የኦነግ የጦር አበጋዞች መንግሥትን አንተክልም!!!›› ፀ/ት ፂዮን ዘማርያም

የኢትዮጵያ ሠራተኞች ፓርቲ (ኢሠፓ)(1984-1991)፣ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት)(1975-2020)፣ ብልጽግና ፓርቲ (2018-?)

የትህነግ የጦር አበጋዞች መንግሥት ነቅለን፣ የኦነግ የጦር አበጋዞች መንግሥት አንተክልም!!! የወያኔና የኦነግ አራጆች አንድም ሁለትም ናቸውና!!! የቅኝ ግዛትና የአማራ የጨቆኝ ገዢነት የወያኔና ኦነግ የውሽት ትርክት፣ የአማራውን ህዝብ በየቦታው  እንዲታረድ አስደርጎታል፡፡ በሃገሪቱ የዘርና ኃይማኖት የዘር ፍጅት (ጆኖሳይድ) ወንጀለኞች እንደ አሸን ለመፈልፈላቸው ተጠያቂው ወያኔ፣ ኦነግና የብልፅግና ፓርቲ ናቸው፡፡ የአማራው ህዝብ በህዝባዊ ትግሉ የህወሓት የጦር አበጋዝ መንግሥት ከስር መሠረቱ መንግሎ በመጣል የተነጠቀውን ግዛት በደሙ አስመልሶል፡፡ የወያኔን ህገመንግሥት ቀይሮ ሁሉም የተሳተፈበት አዲስ ህገመንግስት አርቅቆ አንቀፅ ሠላሣ ዘጠኝን፣ የዘር ፌዴራሊዝምን በሃቀኛ ሳይንሳዊ ፌዴራሊዝም መንግሥታዊ አስተዳደራዊ መዋቅር በመዘርጋት በዘር ላይ የተመሠረተ አገዛዝን በዴሞክራሲያዊ ህዝባዊ አስተዳደር በመተካት እንዲሁም የህዝቡ  ጂኦ ፖለቲካል አስተዳደራዊ አወቃቀር በዘር ሳይሆን ጆግራፊያዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ባህላዊ ሁኔታዎች ላይ ያተኮረ ተደርጎ ወሰንና ድንበር በማጥፋት ማንኛውን ኢትዮጵያዊ በአሰኘው ቦታ ተዘዋውሮ የመስራት ኃብትና ንብረት የማፍራት መብቶቹ ተጠብቆለት በሠላምና ፍቅር በአንድነት እንዲኖር ማድረግ መብቶቹ እንዲጠበቁለት ማድረግ ያስፈልጋል እንላለን፡፡ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በህይወት የመኖር መብቱ ተጠብቆለት ግብር ከፋዩ ህዝብ ደሞዝ የሚቆረጥለት መንግሥት በሃገሪቱ የህግ ሉዓላዊነት በመከላከያ ሠራዊትና ፖሊስ ኃይል የማስከበር ኃላፊነትና ተጠያቂነት ከዚህ ጊዜ በኃላ ተግባራዊ ካልሆነ ህዝብ የሠቀለውን ማውረድ ከወያኔ ተምሮል እንላለን የወያኔን የዘር አገዛዝ በኦነግ የተረኛነት፣ የዘረኛነት ኦሮሙማ ርዕዬት ለመትከል መሞከር አይቻልም፣ በጦርነቱ የወደቁ ሠማእታት ደም ይጮሃል እንላችሆለን፣  ከእንግዲህ ጨው ለእራስህ ስትል ጣፍጥ እንላለን፡፡ ለዚህ ነው ህወሃት በብርተኛነት ተፈርጆ በኢትዮጵያ ህግ መሠረዝ አለበት የምንለው፡፡ በግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ/ም ህወሓት ሥልጣን  በያዘ ማግስት   የኢትዮጵያ ሠራተኞች ፓርቲ (ኢሠፓ)ን በህግ በማፍረስ የመምረጥና መመረጥ ህገመንግስታዊ መብቱን አግዶ የበተነውና ለፍርድ ያቀረበው ልብ ሊባል ይገባል፡፡

የኢትዮጵያ ሠራተኞች ፓርቲ፣(1984-1991)፤ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (1975-2020)፤ብልፅግና ፓርቲ (2018-?)

የኢትዮጵያ ሠራተኞች ፓርቲ (Workers’ Party of Ethiopia) ኢሠፓ በግራ ዘመም የማርክሲስት ሌኒኒስት የኮምኒስት ርዕዮት ተከታይነት ሴፕቴምበር 12 ቀን 1984 እኤአ በኢትዮጵያ ምድር በሊቀመንበር መንግሥቱ ኃይለማርያም  ተወለደ፣ተመሰረተ፡፡ ኢሠፓ ከሰባት ቆይታ በኃላ በህወሓት/ኢህአዴግ ተሸንፎ  በሜይ 21 ቀን  1991እኤአ በህግ ታገደ፡፡  ኮነሬል መንግሥቱ ኃይለማርያም ኢትዮጵያን ለአስራ ሰባት አመታት በግፍ ገዝተዋል፡፡

ኢሠፓ ብቸኛ ፓርቲ በመሆን የኢትዮጵያ ዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኢትዮጵያ (People’s Democratic Republic of Ethiopia)  መግዛት ጀመረ፡፡ ኢሠፓ ሰማንያ ሽህ አባላቶች የነበሩት ሲሆን ከመቶ ሃያ ሦስት የማዕከላዊ ኮሚቴ አባሎች ውስጥ ሰባ ዘጠኙ  የመከላከያ ሠራዊትና የፖሊስ ኃይል አባሎች ነበሩ፡፡ ከዚህም ውስጥ ሃያዎቹ የደርግ አባላት የነበሩ ናቸው፡፡ (1)

 • የኢትዮጵያ ሠራተኞች ፓርቲ በነፃ እርምጃና በቀይ ሽብር ብዙ ሽህ ወጣቶችን በመግደል፣ በተለይም የተቃዋሚ ፓርቲ የነበሩ የኢህአፓ፣ መኢሶን፣ ኢዲዩ ወዘተ አባሎችን በግፍ በመግደል ተወንጅለው ነበር፡፡
 • የኢትዮጵያ ሠራተኞች ፓርቲ ስልሣ የቀኃሥ ባለሥልጣኖችን፣ ሚኒስትሮችን፣ ጀነራል መኮንኖችን፣ ዲፕሎማቶችንና አምባሳደሮችን፣ ረሽኖ በአንድ ጉድጎድ በመቅበር ክስ ተወንጅሎ ነበር፡፡
 • የኢትዮጵያ ሠራተኞች ፓርቲ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትና ፖሊስ ኃይል ጀነራል መኮንኖችን መፈንቅለ መንግሥት ክስ ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ በግፍ በመረሸን ተወንጅሎ ነበር፡፡

 

ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ፤ የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ግንባር (Tigray People’s Liberation Front) በግራ ዘመም የማርክሲስት ሌኒኒስት የኮምኒስት ርዕዮት ተከታይነት በፌብሪዋሪ 18 ቀን 1975 እኤአ በኢትዮጵያ ምድር በደደቢት በርሃ ተመሠረተ፡፡  ህወሓት በሊቀመንበር መለስ ዜናዊ ሃያ ሰባት ዓመታት አገዛዝ ቆይታ በኃላ በህወሓት/ኢህአዴግ ተሸንፎ  በኖቨምበር  24 ቀን  2020 እኤአ በህግ ሊታገደ ይገባል እንላለን፡፡  ህወሓት በኢህአዴግ ምርጫ ህወሓት ተሸንፎል፣ በብልፅግና ፓርቲም ምሥረታ ራሱን አግልሎል፡፡  በኖቨምበር  24 ቀን  2020 እኤአ በህግ ሊታገድ የሚያስችሉ የሃገር ክህደት ወንጀሎች በመፈጸም በህግ ተሠርዞል፡፡ የትግራይ ህዝብ ከህወሓት በስብዓዊ ጋሻነት አፈናና ጭቆና ከተያዘበት የባርነት ሠንሠለት ከአርባ ስድስት አመታት በኃላ ነፃ ወጥቷል፡፡

 • የትግራይ የጦር አበጋዞች ሽብርተኛ መንግሥት በሃያ ሰባት አመታት የግፍ አገዛዙ ዘመን በድብቅ ገድሎ የቀበራቸው ሠማዕታት ከጅምላ መቃብሮቻቸው አፈርና ድንጊያ ፈንቅለው ነፃ ይወጣሉ፣ በሃለዋ ወያኔ እስር ቤቶች የታሠሩ እስረኞች ይፈታሉ፣ የወያኔ ጁንታ ወንጀለኞች ለፍርድ ይቀርባሉ፣ የህወሓት፣ተባባሪ የነበሩ ድርጅቶች ብአዴን፣ኦህዴድና ደኢህድን ወንጀለኛ ሹማምንት ካድሬዎችም ለፍርድ አብረው ይቀርባሉ፡፡ ወያኔ ባፀደቀው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ሃያ ስምንት ‹‹›ኢትዮጵያ ባፀደቀቻቸው አለም አቀፍ ስምምነቶች እና በሌሎች የኢትጵያ ህጎች በሰው ልጅ ላይ የተፈፀሙ ተብለው የተወሰኑትን ወንጀሎች፣ የሰው ዘር የማጥፋት፣ያለፍርድ የሞት ቅጣት እርምጃ የመውሰድ፣ በአስገዳጅ ሰውንየመሰወርዌም ኢሰብዓዊ የድብደባ ድርጊቶችን በፈፀሙ ሰዎች ላይ ክስ ማቅረብ ቤርጋ አይታገድም፡፡ በሕግ አውጭው ክፍልም ሆነ በማንኛውም የመንግስት አካልውሳኔዎች በምህረት ወይም በይቅርታ ኤታለፍም፡፡››(2)
 • በጥቅምት 24 ቀን 2013ዓ/ም የትግራይ የጦር አበጋዞች መንግስት ዶክተር ደብረፂዮን ገብረማርያም በትግራይ ውስጥ የሚገኘውን ኢትዮጵያን የፌዴራል መንግሥት የሰሜን ዕዝ መከላከያ ሠራዊት ላይ የመሣሪያ ጥቃት በመፈፀም የአማራ ተወላጅ ወታደሮችን በመግደል፣ የሃገሪቱን የጦር መሣሪያ ግምጃ ቤት በመማረክ የተራ ወንበዴ ሥራ ሰርቶል፡፡
 • የትግራይ የጦር አበጋዞች መንግሥት የህወሓት ሠራዊት በማይካድራ በአማራ ተወላጆች ላይ በገጀራ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈፅሞል፣ ብዛታቸው ከ350 እስከ 500 ሰዎች ይገመታል፡፡ የሰሜን ዕዝ መከላከያ ሠራዊት አባሎችን በተለይም የአማራ ተወላጆችን በመግደልና መሳሪያውን በመዝረፍ ዳግም ወደ ሥልጣን መንበራችን እንመለሳለን በሚል የንፁሃን ዜጎችን ህይወት ቀጥፈዋል፡፡  የማይካድራ የአማራ ዘር ጭፍጨፋ በተባበሩት መንግሥታት በጦር ወንጀልነት ሊያስከስሳቸው እንደሚችል ተገልፆል፡፡
 • የትግራይ የጦር አበጋዞች ሽብርተኛ መንግሥት 13 ቀን ህዳር 2020 እኤአ በአማራ ክልል ዋና ከተማ ባሕር ዳር እንዲሁም በቅርብ ርቀት በምትገኘው የጎንደር ከተማ ውስጥ የሚገኙ አየር ማረፊያዎችን ኢላማ ያደረገ የሮኬት ጥቃት መፈጸሙን የኢትዮጵያ መንግሥት ገለጸ። በሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ ውስጥ የተከሰተውን ቀውስ ተከትሎ በክልሉ የተጣለውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በተመለከተ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት መረጃ የሚሰጠው ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀው በሮኬት ጥቃቱ በአውሮፕላን ማረፊያዎቹ አካባቢ “መጠነኛ ጉዳት” መድረሱን አመልክቷል። ከፌደራል መንግሥቱ ጋር ግጭት ውስጥ የሚገኘው ህወሓት ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ ጥቃቱን መፈጸማቸውን ለትግራይ ቴሌቪዥን ተናግረዋል።
 • የትግራይ የጦር አበጋዞች ሽብርተኛ መንግሥት የኤርትራ ዋና መዲና የሆነችውን አስመራ ከተማን ሦስት ሮኬት አስወንችፎ መቶል፡፡ ወያኔ በአሜሪካ መንግሥትና በሌሎችም ድርጊቱ ተወግዞል፡፡ (3)

 

ብልጽግና ፓርቲ (Prosperity Party) ብልፅግና ፓርቲ በመደመር ርዕዮት ተከታይነት በዲሴምበር  1 ቀን 2019 እኤአ በኢትዮጵያ ምድር በሊቀመንበር ዶክተር ዐብይ አህመድ ተመሰረተ፡፡ ብልፅግና ፓርቲ  በህወሓት/ኢህአዴግ በድምፅ ብልጫ አሸንፎ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ምንግሥት በትረ-ሥልጣን የጨበጠ ፓርቲ ነው ፡፡ “The Prosperity Party (Amharic: ብልጽግና ፓርቲis a political party in Ethiopia established on December 1, 2019 as a successor to the Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front (EPRDF) by incumbent Prime Minister Abiy Ahmed. The merger into a countrywide party is part of Abiy’s general policy of distancing the country’s politics from ethnic federalism, and it will thus run for the first time in the 2021 general election. The Prosperity Party was formed through the merging of three former EPRDF member parties, the Amhara Democratic Party (ADP), the Oromo Democratic Party (ODP) and the Southern Ethiopian People’s Democratic Movement (SEPDM). The Afar National Democratic Party (ANDP), the Benishangul-Gumuz People’s Democratic Unity Front (BGPDUF), the Ethiopian Somali People’s Democratic Party (ESPDP), the Gambela People’s Democratic Movement (GPDM) and the Hareri National League (HNL) were also included in the merger.[6] (4)

ለብልፅግና ፓርቲ ዶክተር ዐብይ አህመድ ህግና ደንብ አስከብር፣ በእኩልነት፣ በፍቅርና በአንድነት እንድታስተዳድር ፈጣሪ ይርዳህ፡፡ የኦሮሙማ ተራኛነትና ዘረኛነት ሰሜትን እንድትጠየፍ ይሁን!!!

በኢትዮኤርትራ ጦርነት ጊዜ በትግራይ ውስጥ የተከማቸውን  የሃገሪቱ የጦር መሣሪያ ሰባ በመቶ የሚሆነውን የጦር ክምችቶን ማውደሞን ዶክተር አብይ አህመድ  አብስሮናል፡፡ በመላ ሃገሪቱ በተደጋጋሚ በሚከሰቱት ግጭቶችና የዘር ፍጅት ከክልሌ ውጣ፣ ህዝብ በነፃነት ተንቀሳቅሶ መስራት አልቻለም፡፡ ሃገሪቱ በጦር አበጋዞች የክልል መንግሥቶች  የድንበር ግጭት የተነሳ ወደማያባራ የእርስ በእርስ ጦርነት ለመሸጋገር ክልሎች ካራ እየሳሉ ይገኛሉ፡፡ የትግራይ ክልል 250000 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሽህ) ልዩ ሓይል፣ የአማራ ክልል 300000 (ሦስት መቶ ሽህ) ልዩ ኃይል፣ የኦሮሚያ ክልል 400000 (አራት መቶ ሽህ) ልዩ ኃይል፣ የሱማሌ ክልል 40000 (አርባ ሽህ በአብዲ ኢሌ ሄጎ ኃይል)፣ የጋምቤላ፣ ቤኒሻንጉል፣ ሃረሪ፣ አፋር፣ ደቡብ (ሲዳማ ክልል አንድ ሽህ ልዩ ኃይል)፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት 250000(ሁለት መቶ ሃምሳ ሽህ) ይገመታል፡፡ ሁሉም ክልሎች የራሳቸው ሚሊሽያና ፖሊስ ኃይል በተጨማሪ አላቸው፡፡  ይህ የዕለት ተዕለት ሥራችን ሆኖ ምርት የማያመርት እልፍ ልዩ ኃይል ጥገኛ ተዋሲያንና ሰባት ሚሊዮን የኢህአዴግና ብልፅግና ፓርቲ ጥገኛ ተዋሲያን መጅገር ካድሬዎች ባሉበት አገር የኢኮኖሚ እድገት አይታሰብም፡፡

የኢፌዲሪ ሕገ-መንግሥት የክልል ሥልጣንና ተግባር ‹‹የክልሉን የፖሊስ ኃይል ያደራጃል ፣ይመራል፣ የክልሉን ሰላምና ጸጥታ ያስጠብቃል፡››  ይላል አንቀጽ 52፡፡ በህገ-መንግሥቱ  መሠረት ክልሎች የፖሊስ ሠራዊት ኃይል ብቻ ይኖራቸዋል ማለት ነው፡፡ የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ( ትህነግ) ህገመንግሥቱ በመጣስ ክልሎች  ልዩ ኃይል እና የሚሊሻ አደረጃጀቶች  እንዲኖራቸው አደረገ፣ ቀስ በቀስ እየተጠናከሩ በመሄድ በክልሎች መኃል ተጨማሪ ኃይል የማሰባሰብ ክልሎች እርስበእርሳቸው የጎሪጥ እንዲተያዩ አደረጋቸው፡፡ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትን በዘርና በብሔር አደረጃጀት ከፋፈለው፣ ሸነሸነው፡፡ ወያኔ የሠራዊቱን  ሃገራዊ ፍቅሩንና ብሄራዊ ክብሩን በማዋረድ ሠራዊቱን በዘርና ኃይማኖት ፍጅት ውስት ተሳታፊ እንዲሆን በመቀስቀስና የዘር ጥላቻ ፕሮፓጋንዳ በመንዛት  ሃገሪቱን እንደ ሶሪያ፣ የመን፣ ሊቢያ ሊያፈርሳት እየጣረ ይገኛል፡፡ የወያኔ የፖለቲካ ሴራ ለስልጣኑ ሲል ሃገር በማፍረስ  ሠራዊቱን  ተባባሪ ማድረግ አልተቻለውም፡፡ ትግራይ ክልል የሚኖር የኢትዮጵያ ሠራዊት የወያኔ ተባባሪ አይሆንም የወያኔ መሪዎችን አስሮ ለፌዴራል መንግስት እንደሚያስረክባቸው ምንም ጥርጥር የለንም፡፡

‹‹የጎሳ ፖለቲካ ጡዘት ሰማይ በነካበት እንደ ኢትዮጵያ አይነት አገር ውስጥ በብሔር የተዋቀረ የክልል ታጣቂ ልዩ ኃይል ወይም ሚሊሻ ማደራጀት ማለት የተጠመደ ፈንጅ በጀርባ አዝሎ እንደመዞር ነው። ክልሎች በአገር ውስጥ ያሉ አገሮች ሆነው ተዋቅረዋል። በዛ ላይ አወቃቀራቸው ቋንቋና ብሔርን መሰረት ያደረገ ነው። የብሔር ፖለቲካው እያመሳት ላለች አገር በብሔር የተደራጁ ታጣቂ ኃይሎች እያሰለጠኑ እና እያስታጠቁ በየክልሉ ማስቀመጥ ካየነው በላይ ብዙ ግፍ እንድናይ እና ኢትዮጵያንም በቀላሉ ወደ ዘር ተኮር ግጭት ከመውሰድም በላይ የአክራሪ ቦድኖች መፍለቂያነት እና ወደ ሽብር ቀጠና ሊለውጣት ይችላል። ከወዲሁም አንዳንድ ምልክቶች በግላጭ እየታዩ ነው፤

በክልሎች መካከል ያለው ውጥረት እና ትከሻ መለካካት በየጊዜው ግጭቶችን አስከትሏል። አሁንም ተፋጠው፣ ጉድጓድ ምሰው እና ቃታ ስበው ለፍልሚያ ቀን የሚጠብቁ አሉ። ለዚህም የትግራይና የአማራ ክልል ፍጥጫ ጥሩ ማሳያ ነው።››

 • ከክልል ፖሊስ በስተቀር ያሉ የክልል ልዩ ኃይል እና የሚሊሻ አደረጃጀትች ሙሉ በሙሉ ከክልሎች እጅ አውጥቶ በፌደራል መዋቅር ስር ማድረግ፣
 • በብሔር የተዋቀረውን የጸጥታ አስከባሪ ኃይል ሙሉ በሙሉ በመበታትን ወደ ሁሉም የአገሪቷ ክፍል ማሰባጠር እና በእያንዳንዱ ክልል ውስጥ ያለው ታጣቂ ኃይል ከሁሉም ብሔር የተወጣጣ እንዲሆን ማድረግ፣
 • በየክልሉ ያለውን ስብጥር ኃይልን በበላይነት የሚመሩትንም አዛዦች እንዲሁ በተሰባጠረ መልኩ ማዋቀር፣
 • ይህን ኃይል በቂ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በመስጠት አይምሯቸው ውስጥ ያለውን የብሔረተኝነት ስሜት በሂደት እንዲቀይሩና ያለመድሎ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ደህንነት ዘብ እንዲቆሙ ማድረግ።

 

ምንጭ/ Reference

(1) https://en.wikipedia.org/wiki/Workers%27_Party_of_Ethiopia

(2) የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ሃያ ስምንት ገፅ 18

(3) https://en.wikipedia.org/wiki/Tigray_People%27s_Liberation_Front

(4) https://en.wikipedia.org/wiki/Prosperity_Party

 

Leave a Reply