የትሕነግ ሴራ ባላባት አቦይ ስብሃት ነጋን ጨምሮ በቁጥጥር ስር የዋሉ ዘጠኝ የትሕነግ ጁንታው አመራሮች አዲስ አበባ ገቡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 1 ቀን 2013 ዓ.ም…

የትሕነግ ሴራ ባላባት አቦይ ስብሃት ነጋን ጨምሮ በቁጥጥር ስር የዋሉ ዘጠኝ የትሕነግ ጁንታው አመራሮች አዲስ አበባ ገቡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 1 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የጥፋት ስትራቴጂስቱና ዋነኛው የጁንታ መሪ ስብሃት ነጋን ጨምሮ በቁጥጥር ስር የዋሉ ዘጠኝ የትሕነግ ጁንታው አመራሮች አዲስ አበባ ገብተዋል። የሀገር መከላከያ ሰራዊት የጥፋት ስትራቴጂስቱና ዋነኛው የጁንታ መሪ ስብሃት ነጋን ጨምሮ ሌሎች የጥፋት ቡድኑ አመራሮች በቁጥጥር ስር ማዋሉን መግለጹ ይታወሳል። የከሃዲው አመራሮች የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ የፌደራል ፖሊስና ሌሎች የፌደራል ጸጥታ ተቋማት ባደረጉት ፍተሻና አሰሳ ከተደበቁበት ለሰው ልጅ እጅግ አስቸጋሪ መሆኑ በተነገረለት የተከዜ ሰርጥ ዝንጀሮ ገደል ውስጥ ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት ተብሏል። የጥፋት ቡድኑ አመራሮችን ለመከላከል በአካባቢው ጥበቃ ላይ የነበረ የቡድኑ ታጣቂ ሀይል መደምሰሱንም መከላከያ ማሳወቁ ይታወሳል። መከላከያ ሰራዊት በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጹ እንዳጋራው በማዕከላዊ ትግራይ አዴር አዴት በሚባል አካባቢ ልዩ ስሙ ጅራ በሚባል ጥልቅ ገደል ውስጥ ተደብቀው የተገኙ የከሃዲው ጁንታ ቡድን ከፍተኛ አመራሮች:_ 1- አቶ ስብሃት ነጋ /አቦይ ስብሃት/ – የቡድኑ ቁንጮ የሴራ ወጣኝ 2- ወ/ሮ ቅዱሳን ነጋ /የስብሃት ትንሽ እህት/ – የክልሉ አፈጉባኤ የነበረች 3- አቶ ቴዎድሮስ ሀጎስ – የመለስ ዜናዊ አካዳሚ ፕሬዝዳንት የነበረ 4- አቶ አባዲ ዘሞ – በሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበረ እና የህወሓት የፖለቲካ ክንፍ መሪ የነበረ 5- አቶ ወልደጊዮርጊስ ደስታ – የክልሉ የመንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ሀላፊ የነበረ 6- አቶ ገብረመድህን ተወልደ – የክልሉ የንግድ ቢሮ ሀላፊ የነበረ 7- ዶ/ር ሰለሞን ኪዳኑ – የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ሀላፊ የነበረ 8- ወ/ሮ ምህረት ተክላይ – የክልሉ ምክርቤት የህግ ጉዳዬች አማካሪ የነበረች 9- አቶ ተክለወይኒ አሰፋ – የማህበር ረድኤት ትግራይ /ማረት/ ስራ አስኪያጅ የነበሩ ናቸው። የመከላከያ ሠራዊት ባደረገው ኦፕሬሽን አቦይ ስብሃትን ጨምሮ ሌ/ኮ አፀዱ ሪች ፣ ኮ/ል ክንፈ ታደሠ ፣ኮ/ል የማነ ካሕሳይ ፣ አቶ አስገደ ገ/ክርስቶስ ፣ አቶ አምደማርያም ተሠማ ፣ ኮማንደር በረሄ ግርማ በቁጥጥር ስር መዋላቸውንና የሜ/ጀነራል ሀየሎም አርአያ ባለቤት የነበረችው ወ/ሮ አልጋነሽ መለስ ከገደል ላይ ወድቃ መሞቷ መረጋገጡን ትናንት ለሚዲያዎች ይፋ መደረጉ አይዘነጋም።

Source: Link to the Post

Leave a Reply