የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ከምደባ ውጪ ባሉ መርሃግብሮች የሚቀበሏቸውን የተማሪዎች የትምህርት ማስረጃዎቻቸውን እንዲያረጋግጡ ጠየቀ፡፡ ባለስልጣኑ ለሁሉም የመንግ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/araH3pOnUVXXJyZTRiUU0SGJRDOyzh-NWSa6AgvOFJbndqtMcKNNcV9UyUB_mtPxa3WHDoMl4Y0-gvX9nFiUe1yhgQsr2AU9gIBTT35BYghwThRg8RW3Rwkqpm6_UyzA59MmEPUmOfsQfYRDt4BjxmSywSt8ay6vJowgLW9ytTL0HLYQ6c3sBWBmaqQaKsQEIivEEyJ-f7wgG8m54f9GyRCDaZ-Bh2jQsLLR3hWm98Bjg3ZiDuI-KspjWZuRU2rWze1ya2wbQ7yLz3Tg1KjN0ezdxCcoS38cvMhWo-JVc6VD6XRObGzdw0VUq6MuYgDiy_UFJAinkJbvPIJiuNvodg.jpg

የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ከምደባ ውጪ ባሉ መርሃግብሮች የሚቀበሏቸውን የተማሪዎች የትምህርት ማስረጃዎቻቸውን እንዲያረጋግጡ ጠየቀ፡፡

ባለስልጣኑ ለሁሉም የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በፃፈው ደብዳቤ ትምህርት ተቋማቱ ከመንግስት ምደባ ውጪ በማታ እና በርቀት ትምህርት በራሳቸው መልምለው እንዲሁም የተለያዩ መስሪያ ቤቶች በአቅም ግንባታ ሲባል የሚልኳቸውን ተማሪዎችን እንደሚቀበሉ አስታውሷል፡፡

በመሆኑም ከዚህ በሁዋላ በሚኖር የተማሪዎች ቅበላ ወቅት ሶስት ጉዳዮችን ልዩትኩረት ሰጥቶ መመዝገብ እንደሚገባ አሳስቧል፡፡
በተጨማሪም ፡-
– በግሉ አልያም በመስሪያ ቤት ለድህረ ምረቃ ለመመዝገብ የሚቀርቡ ማመልከቻዎች ከባለስልጣኑ መስሪያ ቤቱ ህጋዊነት እና ትክክለኛነት የተረጋገጠ መሆኑን ማጣራት

– በማንኛውም ደረጃ ከውጭ የተገኙ የትምህርት ማስረጃዎች በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የአቻ ግመታ የተሰጣቸው መሆን እና
– የቴክኒክ እና ሙያ የትምህርት ማስረጃዎችም በሚመለከተው አካል ህጋዊነታቸው የተረጋገጠ መሆን እንደሚገባው አሳስቧል፡፡

አያይዞም የሃሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎች ተበራክተዋል ተብሎ ስለሚታመን፤ በትምህርት ተቋማቱ የሚሰሩ ሰራተኞችን የትምህርት ማስረጃዎቻቸውን እንዲያረጋግጡ ይሁን ሲል አሳስቧል፡፡

ባለስልጣኑ የተሰጠውን ተልእኮ ያለ ትምህርት ተቋማቱ ማሳካት እንደማይችል ያስታወሰ ሲሆን ዩኒቨርስቲዎች እያበረከቱ ላለውም አስተዋፅኦ እውቅናን እንደሰጠ የላከልን መረጃ ያመለክታል፡፡

ሚያዝያ 13 ቀን 2014 ዓ.ም

አብዱልሰላም አንሳር

Source: Link to the Post

Leave a Reply