የትራምፕ ተቀናቃኝ ከውድድር ወጥቻለሁ እርሳቸውንም እደግፋለሁ አሉየፍሎሪዳ ገዥ ሮን ዲሳንተስ የሪፐብሊካን እጩ ሆነው ለፕሬዝዳንትነት ለመወዳደር ከፍተኛ ፉክክር ላይ የቁዩ ቢሆንም ራሳቸውን…

የትራምፕ ተቀናቃኝ ከውድድር ወጥቻለሁ እርሳቸውንም እደግፋለሁ አሉ

የፍሎሪዳ ገዥ ሮን ዲሳንተስ የሪፐብሊካን እጩ ሆነው ለፕሬዝዳንትነት ለመወዳደር ከፍተኛ ፉክክር ላይ የቁዩ ቢሆንም ራሳቸውን ከምርጫው ማግለላቸውን አሳውቀዋል፡፡

የትራምፕ ከፍተኛ ተቀናቃኝ ዲሳንተስ ከፎክክሮ ራሳቸውን ማውጣት ብቻ ሳይሆን ትራምፕን እንደሚደግፉ ተናግረዋል።

የዲሳንተስ ለትራምፕ ድጋፍ መስጠት በውድድሩ ከፍተኛ ለውጥ ያመጣል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።

ዲሳንተስ በቃኝ ያሉት ነገ ማክሰኞ በኒው ሐምፕሻየር ግዛት ድምጽ ሊሰጥ በሚጠበቅበት ዋዜማ ነው።

ትላንት እሑድ ከሰዓት የምረጡኝ ቅስቀሳ በኒው ሐምፕሻየር ግዛት ሲያደርጉ የነበሩት ትራምፕ የተቀናቃኛቸውን የዲሳንተስን ከውድድር መውጣት ይፋ ሲያደርጉ ደጋፊዎቻቸው በሆታ ደስታቸውን ገልጸውላቸዋል።

ትራምፕ ከአፍታ በኋላ ዲሳንተስ ብርቱ ሰው ነበር፤ ብዙ ርቀት ሄዷል፤ ሊደነቅ ይገባል በማለት አዎንታዊ አስተያየት ሰጥተዋል።

ትራምፕ ለወራት ተፎካካሪያቸው ዲሳንቲስን “ቀሽም፣ አስቀያሚ፣ ከንቱ፣ እኔ ከትቢያ አንስቼ ሰው ያደረኩት፣ የእናት ጡት ነካሽ . . . ” እያሉ ሲያብጠለጥሏቸው እንደነበር ይታወሳል።

በርካታ የሪፐብሊካን ደጋፊዎች ለቢቢሲ እንደተናገሩት ዲሳንተስ ጥሩ እጩ ቢሆንም አሁን የሱ ጊዜ አይደለም ብለዋል።

የትራምፕ የዋይት ሐውስ ጉዞ ምናልባት እየቀረቡባቸው ባሉ በአራት መዝገብ በተዋቀሩ 91 ተደራራቢ ክሶች የማይጨናገፍ ከሆነ ሊሰምር የተቃረበ ይመስላል።

ጥር 13 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Telegram (https://t.me/ethiofm107dot8

Source: Link to the Post

Leave a Reply