የትራንስፖርት ሚኒስቴር ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር እያደረገ ነው

የትራንስፖርት ሚኒስቴር ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር እያደረገ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የትራንስፖርት ሚኒስቴር በዘርፉ የሚታዩ ችግሮችን ለመቅረፍ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በአዳማ እየመከረ ይገኛል።

በውይይቱ ለማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እድገት ዋነኛ ሚና የሚጫወተው የትራንስፖርት ዘርፍ የዜጎችን ህይወት ለህልፈት እየዳረገ መሆኑም ተነስቷል።

የአሽከርካሪዎች ብቃት ማነስ፣ የስነ ምግባር ችግር እና የተሽከርካሪዎች የቴክኒክ ጉድለት በኢትዮጵያ ለሚደርሱ የትራፊክ አደጋዎች ዋነኛ ምክንያቶች ናቸው ተብሏል።

በተያያዘም የመንገድ ደህንነትና የትራፊክ ቁጥጥርን ለማጠናከር የአቅም ግንባታና የማነቃቂያ ስልጠና ለትራፊክ ፖሊሶች እየተሰጠ ይገኛል።

በቆንጂት ዘውዴ

The post የትራንስፖርት ሚኒስቴር ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር እያደረገ ነው appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply