የትራንስፖርት ባለስልጣን በ2014 ዓ.ም ባወጣው ታሪፍ መሰረት ተግባራዊ ባላደረጉ መስመሮች የታሪፍ ማሻሻያ መደረጉን የከተማዋ አዉቶብሰ አገልግሎት አስታወቀ።የአዲስ አበባ ከተማ የህዝብ…

የትራንስፖርት ባለስልጣን በ2014 ዓ.ም ባወጣው ታሪፍ መሰረት ተግባራዊ ባላደረጉ መስመሮች የታሪፍ ማሻሻያ መደረጉን የከተማዋ አዉቶብሰ አገልግሎት አስታወቀ።

የአዲስ አበባ ከተማ የህዝብ ማመላለሻ አዉቶብስ የኦፕሬሽን ምክትል ሃላፊ አቶ አስቻለዉ መቅጫ በ2014 ዓ.ም የተሻሻለዉ ታሪፍ ሳይተገበረ መቆየቱን ተናግረዋል፡፡

የታሪፍ ማሻሻያዉን ያልተገበሩ መስመሮች ተግባራዊ እንዲያደርጉ መደረጉን ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል ።

በታክሲዎች ላይ በዙ ጊዜ የታሪፍ ለውጥ ቢደረግም በህዝብ ማመላለሻ አውቶብሶች ላይ ግን ሳይደረግ ቆይቷል ብለዋል ።

በመሆኑ የአዲስ አበባ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብሶች የትራስፖርት ባለስልጣን በ2014 ዓ.ም ባወጣው ታሪፍ መሰረት ተግባራዊ ሳይደረግ የቆየው ህግ ነው ተግባራዊ የሆነው ብለዋል።

ከነዚህም የታሪፍ ማሻሻያ ከተደረገባቸው የህዝብ ማመላለሻ ባሶች መካከል ከመገናኛ ወደ ፈረንሳይ የሚወስደው 64 ቁጥርር ባስ አንዱ ነዉ ነዉ ተብሏል፡፡
በዚህ መስመር 5 ብር የነበረዉ ታሪፍ በተሻሻለዉ ወደ 10 ብር ከፍ ተደርጓል ነዉ ያሉት፡፡

በተጨማሪም 27 ቁጥር ከሜክሲኮ ወደ ገላን የሚወስደው ባስ፣121 ቁጥር፣ 106 ቁጥር ባስ ሳይስተካከል የቆየ መስመር በመሆኑን በኪሎ ሜትሩ ኢንተርቨል መሰረት የገንዘብ ለውጥ መደረጉን ተናግረዋል ።

በመጨረሻም ይህ አዲስ ታሪፉ ወጥቶ ሳይሆን የትራስፖርት ባለስልጣን በፊት ወጥተው በልዩ ልዩ ምክንያት ተግባራዊ ባልተደረጉ መስመሮች ላይ በኪሎሜትሩ መሰረት የተስተካከለ ነው ብለዋል፡፡

በልዑል ወልዴ
ግንቦት 02 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply