የትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ጭማሪ ተደረገ

ሐሙስ ሰኔ 30 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በነዳጅ እና የተሸከርካሪ መለዋወጫ ጭማሪ ምክንያት የትራንስፖርት ታሪፍ ማስተካከያ መደረጉን የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒሰቴር አስታወቀ።

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከሰኔ 29 ቀን 2014 ጀምሮ የነዳጅ መሸጫ ዋጋ ማስተካከያ ማድረጉ ይታወቃል፡፡

የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒሰቴር የተደረገውን የነዳጅ መሸጫ ዋጋ ማስተካከያ መሰረት በማድረግ የአገር አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ለሚሰጡ ተሸከርካሪዎች ላይ የትራንስፖርት ታሪፍ ማሻሻያ አድርጓል፡፡

የተደረገው የታሪፍ ማስተካከያ፡-

* በደረጃ አንድ በአስፋልት መንገድ ነባር ታሪፍ በሰው በኪሎሜትር 0.5360 ሲሆን፤ አዲሱ ታሪፍ 0.5600 ብር በኪሎሜትር ሆኗል፡፡ ጭማሪ በኪሎ ሜትር 0.0240 ሳንቲም ነው፡፡

– ደረጃ አንድ በጠጠር መንገድ በሰው በኪሎሜትር ነባር ታሪፍ 0.6150 ሲሆን፤ አዲስ ታሪፍ 0.6464 ነው፡፡ ጭማሪ በሰው በኪሎሜትር 0.0314 ሳንቲም ይሆናል፡፡

* ደረጃ ኹለት በአስፋልት መንገድ ነባር ታሪፍ በሰው በኪሎሜትር 0.5120 ሲሆን፤ አዲስ ታሪፍ 0.5420 ነው፡፡ ጭማሪ 0.0300 ሳንቲም፡፡

– ደረጃ ኹለት በጠጠር መንገድ ነባር ታሪፍ በሰው በኪሎሜትር 0.5680 ሲሆን፤ አዲስ ታሪፍ 0.6054 ብር ነው፡፡ ጭማሪ በኪሎሜትር 0.0374 ሳንቲም፡፡

* ደረጃ ሦስት በአስፋልት መንገድ ነባር ታሪፍ በሰው በኪሎሜትር 0.4750 ሲሆን፤ አዲስ ታሪፍ 0.5081 ነው፡፡ ጭማሪ በኪሎሜትር 0.0331 ሳንቲም ነው፡፡

– ደረጃ ሦስት በጠጠር መንገድ ነባር ታሪፍ በሰው በኪሎሜትር 0.5360 ሲሆን፤ አዲስ ታሪፍ 0.5735 ነው፡፡ ጭማሪ በኪሎሜትር 0.375 ሳንቲም ነው፡፡

የታሪፍ ስሌቱ በ100 ኪሎ ሜትር ሲታይ
* በደረጃ አንድ ተሸከርካሪ በ100 ኪሎሜትር ለአንድ ሰው ነባር ታሪፍ በአስፋልት መንገድ ብር 53.60 ሲሆን፤ በአዲሱ ታሪፍ ብር 56.00 ሆኗል፡፡ ጭማሪ በ100 ሊሎሜትር ብር 2:40 ነው፡፡

* በደረጃ ኹለት ተሸከርካሪ በ100 ኪሎሜትር ለአንድ ሰው ነባር ታሪፍ በአስፋልት መንገድ ብር 51.20 የሚያስከፍል ሲሆን፤ በአዲሱ ታሪፍ ብር 54.20 ሆኗል፡፡ ጭማሪ በ100 ኪሎሜትር ብር 3.00 ነው፡፡

* በደረጃ ሦስት ተሸከርካሪ በ100 ኪሎሜትር ለአንድ ሰው ነባር ታሪፍ በአስፋልት መንገድ ብር 47.50 የሚያስከፍል ሲሆን፤ በአዲሱ ታሪፍ ብር 50.81 ያስከፍላል፡፡ ጭማሪ በ100 ኪሎ ሜትር ብር 3.31 ነው፡፡

በመሆኑም ታሪፉ ከላይ በተገለጸው መሰረት ከዛሬ ሰኔ 30 ቀን 2014 ጀምሮ ተግባራዊ መሆን የጀመረ መሆኑን የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒሰቴር አስታውቋል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply