የትራንስፖርት ክፍያከታሪፍ ውጪ አትክፈሉ ! ” የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች ላይ ምንም አይነት የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ አልተደረገም! ” – የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/Y784HOIbxwBIDcermd0JfZiOs9MadY2f8r9Oia2EA-RO2D_W1c7nP4-edSJTlHFvtjfqFCCOZX19b8rbHcffMTdN6jWK05aQpewC57hjXZ6HEyEgBECAqGDx5Hxag80toNVSUGzgbIO13QLyPj6OZQZ6OjNxSLpKurlS4xUGr3laNg3h0x0v9ycuPsZHSduMZit4gOnZ3RfTYu2SKh_mavKsdS2-MFCEab5zwGbQbq3gOcuTUce1zeX8s_C4ieqRoNSYwALJ-xSojl5oxF0pLlLD0l-4IM2IAAcAQaqFJPXSfwwVXh7ocXJvzoZNVWg8nD2aQRCT7dcq3D7aN198uw.jpg

የትራንስፖርት ክፍያከታሪፍ ውጪ አትክፈሉ !

” የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች ላይ ምንም አይነት የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ አልተደረገም! “

– የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር

ከቀናት በፊት የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ ተግባራዊ ማድረጉ ይታወቃል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ ፤ የታለመለት የነዳጅ ድጎማ ተጠቃሚ የሆኑ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎች በሚጠቀሙት ነዳጅ ላይ ምንም ዓይነት የዋጋ ጭማሪ አልተደረገም።

አነስተኛ ገቢ ያላቸው ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ በተዘረጋው ብሔራዊ የታለመ የነዳጅ ድጎማ አሠራር ታቅፈው ህዝቡን እንዲያገለግሉ የተመረጡት የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎች በሚጠቀሙት ነዳጅ ላይ በ2ኛው ምዕራፍ ምንም ዓይነት የዋጋ ጭማሪ አልተደረገም።

ይህም ማለት ቀደም ሲል ይቀርብ በነበረበት የነጭ ናፍጣና ኬሮሲን ዋጋ ብር 40.86 ፣ የቢንዚን ብር 41.25 ነው እየቀረበ የሚገኘው።

በታለመለት የነዳጅ ድጎማ የታቀፉ ተሽከርካሪ አሽከርካሪዎች ቀደም ሲል በወጣላቸው ታሪፍ ሀብረተሰቡን እንዲያገለግሉ ማሳሰቢያ የተሰጠ ሲሆን ህብረተሰቡ ይህን አውቆ መንግስት ካስቀመጠው ታሪፍ ውጪ ባለመክፈል ተባባሪ እንዲሆን ተጠይቋል።

በተጨማሪም ኃላፊነታቸውን በተገቢው መንገድ የማይወጡ አሽከርካሪዎች ሲያጋጥሙ በየደረጃው ላሉ የፀጥታ አካላት ጥቆማ በመስጠት ህብረተሰቡ መብቱን እንዲያስከብር በትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር መልዕክት ተላልፏል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply