ጥናቱ አሁን በሃገሪቱ እየደረሰ ያለውን የትራፊክ አደጋ በተሻለ ሁኔታ ለመቀነስ እንደሚያግዝ፣ የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ተወካይ አቶ መኳንንት ምናሴ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።
80 በመቶ የሚሆነው የትራፊክ አደጋ የሚከሰተው በአሽከርካሪዎች ስህተት ምክንያትነት እንደሆነ የሚናገሩት አቶ መኳንት፣ ይህን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት የትራፊክ ቅጣት ላይ ማሻሻያ ማድረግ ማስፈለጉን ገልጸዋል።
ከፍጥነት ወሰን በላይ የሚያሽከረክሩ አሽከርካሪዎችን ለመቆጣጠር በራዳር የታገዘ የፍጥነት ወሰን ቁጥጥር እየተደረገ እንደሚገኝም አንስተዋል፡፡
አሽከርካሪዎች ጥፋተኛ ሆነው ሲገኙ ቢቀጡም መሻሻሎች ባለመኖራቸው፣ ተጨማሪ ለውጥ የሚያመጡ ጥናቶች መጀመራቸውን ነግረውናል።
በጥናቱ ላይ የትራንስፖርት ሚኒስቴር፣ የትራንስፖርት ቢሮ፣ የመንገድ ድህንነት ፈንድ እንዲሁም የትራፊክ ማኔጅመንት አጀንሲ ተሳታፊ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
በእሌኒ ግዛቸው
ጥቅምት 05 ቀን 2016 ዓ.ም
Source: Link to the Post