የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ የዋጋ ጭማሪ እና የምርት እጥረት እንዳይከሰት የሚቆጣጠር ግብረ ሃይል መቋቋሙ ተነገረ

የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ የምርት እና የሸቀጦች እጥረት እንዳይሰት እየሰራው ነው ሲል የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ አስታውቋል፡፡

ከ 1ሚሊዮን በላይ የምግብ ዘይት በሸማቾች ህብረት ስራ ማህበራት ለገበያ እንዲቀርብ እየተደረገ ነው ያሉት የቢሮ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሰውነት አየለ ናቸው፡፡

በ188 የእሁድ ገበያዎች እና በ3 የገበያ ማዕከላት፤ ቀይ ሽንኩርት ከ45 እስከ 50 ብር በእሁድ ገበያ የሚሸጥ መሆኑን እና የስኳር እጥረት በሸማቾች ላይ እንደማይኖር የገለጹ ሲሆን፤ ነገር ግን በዓልን ምክንያት በማድረግ በምርት እና በሸቀጦች ላይ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ በቢሮ ቁጥጥር ይደረጋል ብለዋል፡፡

ከደንብ ማስከበር፣ ከምግብ እና መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን የተውጣጣው ግብር ሃይል ፤ በዓል አስመልክቶ የምርት እጥረት ፣ ህገወጥ ንግድ እና፣ በምርት እና በሸቀጦች ላይ የዋጋ ጭማሪዎችን የሚቆጣጠር እና አስተዳደራዊ እርምጃ የሚወስድ ይሆናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

እሌኒ ግዛቸው

ሚያዝያ 22 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply