
የትኛውም እንግልት ትግላችንን ይባስ ቢያግለው እንጂ ሌላ ትርጉም የለም በእነ ዶክተር ወንደሰን መዝገብ የተከሰሱ 23 አማራዎች በአገዛዙ ጠባቂዎች ከፍተኛ እንግልት እየደረሰባቸው እንደሆነ ገልፀው፤ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት የሚገኙ 10 አማራዎች ከየትኛውም እስረኛ ጋር እንዳይገናኙ ተደርገዋል። ብቻቸውን የተከለለ አነስተኛ ግቢ ውስጥ የተደረጉ ሲሆን እነሱ ያሉበት ግቢ የሚጠብቁ የአማራ ተወላጅ ጠባቂዎችን ሙሉ ለሙሉ እንደ ተቀየሩ እና ከፍተኛ ስድብና እንግልት እያደረሱባቸው እንደሆነ ታውቋል። የጥበቃ ኃላፊውም ቢሮ ድረስ በመጥራት ማስፈራሪያ እያደረገባቸው እንደሆነ የኢትዮ 251 ሚዲያ ከማረሚያ ቤት ምንጮቹ አረጋግጧል። ነሐሴ 29 ከፍርድ ቤት በሚመለሱበት ወቅት መኪና ውስጥ “አማራ ነን” የሚለውን ዘፈን በመዝፈናቸው የማረሚያ ቤት ፖሊሶች መሳሪያ አቀባብለው ሊተ…ኩሱባቸው እንደነበርና በደቡብ እና በሌሎች ኢትዮጵያውያን አማካኝነት ከመረሸን መትረፋቸው የሚዘነጋ አይደለም። የኢትዮ 251 የማረሚያ ቤት ምንጮች የማረሚያ ቤት አስተዳደር በስብሰባቸው እነዚህን የአማራ ልጆች የሚችሉትን እንግልት እንዲያደርጉባቸው የወሰኑ ሲሆን አመቺ ሰዓት መርጠው ሊያመልጡ ሲሉ ተኩሰን መታናቸው በማለት ለመረሸን ማሰባቸውንም ለማወቅ ችለናል። #ኢትዮ 251 ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- //Youtube:- Ashara Tv – https://www.youtube.com/channel/UC2LZu_N0iOJipVUw3RyR4Ng //https://www.facebook.com/asharamedia24 //ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post