የትግል አጋራችን ግድያ የተሳተፉ አካላት በአስቸኳይ ለፍርድ ይቅረቡ ሲል የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አስታወቀ፡፡ምክር ቤቱ ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው መግለጫ በፖለቲከኛው በ…

የትግል አጋራችን ግድያ የተሳተፉ አካላት በአስቸኳይ ለፍርድ ይቅረቡ ሲል የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አስታወቀ፡፡

ምክር ቤቱ ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው መግለጫ በፖለቲከኛው በቴ ኡርጌሳ ህልፈት ህይወት የተሰማውን ሀዘን ገልፃል፡፡

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤቱ የኦነግ አመራር የነበሩት አቶ በቴ ኡርጌሳ በትውልድ ከተማቸው ህልፈት ሀይወት መሰማቱን በመግለፅ ሀዘኑን ገልፃል፡፡
የሚመለከተው አካልም የፖለቲከኛውን ህወት ያጠፉ ኣካላት ለህግ እንዲቀርቡም ጠይቋል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ሀዘናቸው እየገለፁ ይገኛሉ፡፡
ከነዚህ መካከል ሀዘናቸውን የገለፁት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ኢዜማ ይገኝበታል ኢዜማ የኦነግ ፖለቲካ ኦፊሰር የሆኑት በቴ ኡርጌሳ በመቂ ከተማ ካረፉበት ሆቴል ተወስደው በጥይት ተደብድበው ተገድለው መገኘታቸውን የተለያዩ የዜና አውታሮች እንዲሁም ፓርቲያቸው ካወጣው መግለጫ ለመረዳት ችለናል ብሏል፡፡

እንዲህ አይነት ግድያዎች በዜጎች ላይ ከፍተኛ የሆነ የደኅንነት ስጋትን የሚጭር እንዲሁም ለዜጎች ደኅንነት ሥጋት ምንጭ እንደሚሆን ሊታወቅ ይገባልም ሲል ነው የገለፀው፡፡

በመሆኑም መንግሥት ጉዳዩን በተለየ ትኩረት ተመልክቶ ተጠያቂነትን እንዲያሠፍን አጥብቀን እንጠይቃለን ሲል በላከልን መግለጫ አስውቋል፡፡
እንደ ኢዜማ ሁሉ ሀዘናቸው ከገለፁ ፓርቲዎች መካካል የወሎ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ይገኝበታል፡፡

ፓርቲው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ከፍተኛ አመራር በሆኑት አቶ በቴ ሁርጌሳ ላይ የተፈፀመው ግድያ ትልቅ ሀዘን እና ድንጋጤ ሆኖብናል ብሏል::

እንደዚህ አይነት ግድያዎችን ያልታወቁ ሰዎች የፈፀሙት ግድያ ነው ብሎ በተደጋጋሚ የመንግስትና የተለያዩ የፖለቲካ አቀንቃኝ ታጋዮች ላይ የሚደርስ ጥቃት ማለፉን እንደ ፓርቲያችን ተቀባይነት የሌለው መሆኑን እየገለፅን ግድያው በአፋጣኝ በገለልተኛ አካላት ተጣርቶ ለህዝብ ይፋ እንዲደረግ ሲል አሳስቧል፡፡

አቤል ደጀኔ

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሚያዝያ 01 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcas

Source: Link to the Post

Leave a Reply