የትግራይ ህዝብም የኦሮሞ ህዝብም በኢትዮጵያዊ ማንነቱ ላይ የማይደራደሩ ታላቅ ኢትዮጵያዊ ነዉ:: —————- ወያኔ እና ኦነግ/ኦህዴድ ግን በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ የስነልቦና ቀዉ…

የትግራይ ህዝብም የኦሮሞ ህዝብም በኢትዮጵያዊ ማንነቱ ላይ የማይደራደሩ ታላቅ ኢትዮጵያዊ ነዉ:: —————- ወያኔ እና ኦነግ/ኦህዴድ ግን በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ የስነልቦና ቀዉስ ዉስጥ የተመሰጉ በማንነት ቀዉስ የተመቱ የህሊና ህመምተኞች ናቸዉ::ይሄም የሆነዉ በራሳቸዉ ምርጫ ነዉ:: —————————- ሸንቁጥ አየለ… ———————— መግቢያ —— ወያኔ እና ኦህዴድ/ኦነግ ሁሉ ጊዜ ማምለጫ አድርገዉ የሚያቀርቡት የሞኝ መከላከያ አላቸዉ::እራሳቸዉን የትግራይ ህዝብ ወይም የኦሮሞ ህዝብ ተወካይ አድርገዉ ማቅረባቸዉ ነዉ::ወያኔ ሲተች የትግራይን ህዝብ ስለማትወዱ ነዉ ይላል::ኦነግ/ኦህዴድ ሲተች የኦሮሞን ህዝብ ስለማትወዱ ነዉ ይላል::እዉነታዉ ግን የትግራይ ህዝብም የኦሮሞ ህዝብም ታላቅ ኢትዮጵያዊ ናቸዉ::የኦሮሞ ህዝብ በኢትዮጵያዊነቱ ላይ ተደራድሮ አያዉቅም::የትግራይም ህዝብ በኢትዮጵያዊነቱ ላይ ተደራድሮ አያዉቅም:: ወያኔ እና ኦነግ/ኦህዴድ ግን በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ የስነልቦና ቀዉስ ዉስጥ የተመሰጉ የህሊና ህመምተኞች ናቸዉ::ይሄም የሆነዉ በራሳቸዉ ምርጫ ነዉ::አንዴ ኢትዮጵያዊ ላለመሆን ሲራገሙ::ሌላ ጊዜ ኢትዮጵያዊ ለመሆን ሲዉተረተሩ የሚገኙ አሳዛኝ ፍጡሮች ናቸዉ::ወያኔ የትግራይን ህዝብ አይወክልም::ኦነግ/ኦህዴድም የኦሮሞን ህዝብ አይወክልም::ወያኔ እና ኦነግ/ኦህዴድ የሚወክሉት በራሳቸዉ የጥላቻ ፕሮፖጋንዳ የተቀረጸዉን የስነልቦና ቀዉስ የማንነት ቀዉስ ዉስጥ የተመሰጉ ግራ የተጋቡ የፖለቲካ ነጋዴዎችን ነዉ:: —————————- የኦሮሞ ህዝብ ከአጼ ምኒሊክ ጋር ፍቅር ነዉ::የሸዋ ኦሮሞ አባቶች ስለ አጼ ምኒሊክ አንሰትዉ በታላቅ ፍቅር ሲናገሩ ቢዉሉ አይጠግቡ::ይሄን ዝም ብዬ አይደለም የምጽፈዉ:: በተጨባጭ ስለማዉቀዉ ነዉ::በአንድ ትልቅ የአርሶ አደር ስብሰባ ላይ አንድ የኦህዴድ/ኦነግ ካድሬ”የነፍጠኛ ስርዓት : የሚኒሊክ ስርዓት” እያለ ማለቂያ የሌለዉ ክሱን ሲያቀርብ አንድ ትልቅ የኦሮሞ አባት እጃቸዉን አዉጥተዉ “እኛ እኮ እየኖርን ያለንዉ በኦህዴድ ስርዓት ዉስጥ ነዉ::የኛ የአሁኑ ጥያቄያችን የተሻለ አስተዳደርን ከኦህዴድ ማግኘት ነዉ::አጼ ምኒሊክ እማ ሀገሩን አንድ አድርገዉ አልፈዋል::ምን አርግ ትላቸዋለህ?”ሲሉ ቢናገሩ የተሰበሰበዉ አርሶ አደር በጋራ በሆታ ተነስቶ እንዳጨበጨበም አስታዉሳለሁ:: ችግሩ ያለዉ ህዉሃት ጠፍጥፋ የሰራቻቸዉ ኦህዴድ/ኦነግ ሀይሎች ጋ ነዉ::ኦህዴድ/ኦነግን ወያኔ ምኒሊክን እንዲጠሉ ከሚሊዮን በላይ ሰሚናሮች:ፕሮፖጋንዳዎች እና የሀሰት ትረካዎችን አዕምሯቸዉ ዉስጥ ጭናባቸዋለች::የ አዕምሮ እጥበትም አድርጋባቸዋለች::ወያኔ ይመስላት የነበረዉ ኦህዴዳዉያን/ኦነጋዉያን ምኒሊክን እስከጠሉ ድረስ የህዉሃትን ስልጣን የሚጋፏትም አይመስሏትም ነበር:: ዛሬ ኦነጋዉያን/ኦህዴዳዉያን ወያኔ እንዳስተማረቻቸዉ የአጼ ምኒሊክን ታሪክ ለማደብዘዝ : አጼ ምኒሊክን ከአድዋ ነጥለዉ አድዋን የጎሳ ለማድረግ ግራ ግብት ይላቸዋል::አንዳንዴ ኦህዴዳዉያን/ኦነጋዉያን በእዉነት በጅጉ ያሳዝኑኛል::ኢትዮጵያዊ ለመሆን ምን ያህል ተቸገሩ::ወያኔ ነብሷን አይማራት እና ኦህዴዳዉያንን/ኦነጋዉያንን ከባድ የስነልቦና ፈተና እና የማንነት ቀዉስ ዉስጥ ጥላቸዉ ሄደ:: ምስኪን ወያኔ እራሷ በራሷም ከኢትዮጵያ ታሪክ ጋር ተጣልታ ነዉ ትግል የጀመረችዉ:: ወያኔ እራሷ አባቶቿ ታሪክ ላይ ቆሻሻ ፕሮፖጋንዳ አድርጋ ነዉ ትግሏን ሀ ብላ የቀመረችዉ::ለምሳሌ “ኢትዮጵያ የመቶ አመት ታሪክ ያላት ሀገር ናት::የትግራይ ህዝብ ከኢትዮጵያ ጋር ታሪካዊ ትሥስር የለዉም::አክሱም ታሪካዊ የኢትዮጵያዉያን የመናገሻ ከተማ ነዉ የሚለዉ አማሮች የፈጠሩት ታሪክ እንጅ አክሱም ትንሽ መንደር ነበረች” የሚሉ በሽተኛ ፕሮፖጋንዳዎችን ለራሷ ግታ ግታ ትግል ጀመረች::እግዚአብሄር የለመኑትን አይነሳም እና የኢትዮጵያ መሪ አደረጋት::ወያኔም ግራ እንደገባት የማንነት ቀዉስ ዉስጥ ተመስጋ ከኢትዮጵያዊነት ጋር ሳትታረቅ 27 አመታት ሀገር መራች:: በ2000 ዓም ድንገት የሆነ ነገር ትዝ አላት::ኢትዮጵያዊ ለመሆን አሰበች እና የሚሊኒዮም አከባበር የሚል ፕሮፖጋንዳ ጀመረች::ከዚያም ሳታፍር ኢትዮጵያ የመቶ አመት ታሪክ ነዉ ያላት የሚለዉን ትርክቷን አነሳች:: ኢትዮጵያ የሶስት ሽህ አመታት ታሪክ አላት ብላ ሚሊዬም ስትል 2000 ዓም ን አከበረች::እንዲህ በራስ ላይ መርዝ እየነሰነሱ እራስን በቤንዚን ማቃጠል ማለት ይሄዉ ነዉ::ይሄ እጅግ ታላቅ የስነልቦና ቀዉስ ነዉ::በወቅቱ አንድ የሀገራዊ ፖሊሲ ጥናት መድረክ ላይ ያገኘሁት ትልቅ ባለስልጣን ስለ ሚሊኒዬም ምን እንደማስብ ሻይ እየጠጣን ቢጠይቀኝ “ኢትዮጵያ መቶ አመታት ታሪክ ያላት ሀገር ናት እንጂ 3ሽህ ታሪክ ከዬት አመጣች?” ብዬ መልሼ ብጠይቀዉ ሽሙጤ ገብቶት ፈገግ ያላት ፈገግታ እስካሁን ትዝ ትለኛለች:: የትግራይ ህዝብ በጣም ታላቅ ኢትዮጵያዊ መሰረት ያለዉ ህዝብ ነዉ::ትግራይ በተዘዋወርኩባቸዉ አመታት ዉስጥ አክሱምም ሆነ አድዋ ወይም ሌላ ወረዳዎች ስሄድ ልቤ ትርትር ብሎ የሚያስደነግጠኝ ብዙ ነገር ገጥሞኛል::እህዝቡ ዉስጥ እጅግ ጥልቅ ኢትዮጵያዊነት ነዉ ያለዉ::የወጣቶቹን እና የአርሶ አደሮቹን ስሜት ለመገመት ስልጠና በምሰጥባቸዉ ጊዚያቶች ሁሉ የኢትዮጵያን ጉዳይ ጮክ አድርጌ በማንሳት የኢትዮጵያን ታሪካዊ እሴት ጉዳይ ግንዛቤአቸዉን ስጠይቅ የሚገርም ትልቅ ኢትዮጵያዊ እሴት በህዝቡም በወጣቱም ዉስጥ አለ::ወያኔ ያን ያህል ፕሮፖጋንዳ ቢሰራም የማይደበዝዝ ኢትዮጵያዊነት ህዝብ ይነበባል:: አንዳንድ የወያኔ አነስተኛ ካድሬዎችንም በጓደኝነትም በቀልድም የምጠይቃቸዉ ጥያቄ “እናንተ የትግራይ ህዝብ ከኢትዮጵያዉያን ጋር ታሪካዊ ትሥስር የለዉም ትላላችሁ::ህዝቡ ግን ልክ እንደኔ ዘመዶች ኢትዮጵያን በጥንታዊ ሀገርነቷ ብቻ ሳይሆን የትግራይም ህዝብ የዚህ ጥንታዊ ታሪክ አካል እንደሆነ ይመሰክራል::እናንተ ስለኢትዮጵያ የያዛችሁትን ትርክት ከዬት ነዉ ያገኛችሁት?” ስለ የጠዬቅሁበት ጊዜ አለ:: ሌላዉ ትግራይ ዉስጥ ብዙ ጊዜ ከሚያስደነግጠኝ ነገር በዬወረዳዉ ስሄድ እኔን የሚመሳስሉ ሰዎች እና ዘመዶቼች የሚመሳስሉ ሰዎች በብዛት የማግኘቴ ሚስጢር ነበር::ብዙዎቹንም አብሬአቸዉ ፎቶ እንድንነሳ እየጠዬቅሁ አብሬአቸዉ በርካታ ፎቶዎች ተነስቼአለሁ::አንዳንዴ ብቻዬን በእጅጉ እገረም ነበር::”ወያኔ ይሄን ሁሉ የልዩነት ሀሰተኛ የጥላቻ ታሪክ ሳትጽፍ እና ፕሮፖጋንዳዋን በጥላቻ ላይ ሳትቀምር ለስልጣን መታገል አትችልም ነበር?::መልኩ ሳይቀር እንዲህ የሚመሳሰልን ህዝብ በልዩነት እና በጥላቻ ሳይለያዩ ስልጣን መያዝ አይቻልም?” ብዬ እራስኔ እጠይቃለሁ::ግን የረባም መልስ የለኝም:: የወያኔ ክፋት ግን የትግራይን ህዝብ ከኢትዮጵያዊነት ለመነጠል በመጣር ላይ አልተወሰነም::ወደ መሃል ኢትዮጵያም ስትመጣ እንደ ኦህዴድ/ኦነግ አይነት ጭቃዎችን ጠፍጥፋ በመስራት በጥላቻ ፕሮፖጋንዳ አቡክታ በማበጀት የኦሮሞን ህዝብ ከኢትዮጵያዊነት ለመነጠል ያላደረገችዉ ሙከራ የለም::ወያኔ የትግራይን ህዝብ ከኢትዮጵያዊነት መነጠል እንዳልቻለችዉ ሁሉ ኦነግ/ኦህዴድም የኦሮሞን ህዝብ ከኢትዮጵያዊነት መነጠል አልቻለም:: ሆኖም እራሳቸዉ ወያኔ እና ኦህዴድ/ኦነግ ግን በራሳቸዉ የሀሰት ትርክት እና ፕሮፖጋንዳ በአስተማማኝ ከኢትዮጵያዊነት ተጣልተዋል::ስለሆነም ኢትዮጵያዊ ለመሆን ግራ ግብት ይላቸዋል::ወያኔ የመቶ አመት ታሪክ ያለችዉን ቀልብሳ የ3ሽህ ታሪክ ያላት ኢትዮጵያ በማለት ሚሊኒዬም ስታከብር ስትል ምን አይነት ግራ መጋባት ዉስጥ እና የስነልቦና ዉስጥ እንደምትዘፈቅ አስቡት:: ኦህዴድ/ኦነግም አድዋ የባርነት ታሪክ ነዉ እያለ ፕሮፖጋንዳዉን ሲነፋ ኖሮ ድንገት ተገልብጦ ደግሞ የአድዋን ታሪክ አከብራለሁ ብሎ በመነሳት አድዋን አለ አድዋ መሪ ለማክበር ሲዉተረተር እንዴት ኢትዮጵያዊ ለመሆን እንደተቸገረ አስቡት:: ————————— ወያኔ እና ኦህዴድ/ኦነግ ሁሉ ጊዜ ማምለጫ አድርገዉ የሚያቀርቡት የሞኝ መከላከያ አላቸዉ::እራሳቸዉን የትግራይ ህዝብ ወይም የኦሮሞ ህዝብ ተወካይ አድርገዉ ማቅረባቸዉ ነዉ::ወያኔ ሲተች የትግራይን ህዝብ ስለማትወዱ ነዉ ይላል::ኦነግ/ኦህዴድ ሲተች የኦሮሞን ህዝብ ስለማትወዱ ነዉ ይላል::እዉነታዉ ግን የትግራይ ህዝብም የኦሮሞ ህዝብም ታላቅ ኢትዮጵያዊ ናቸዉ::የኦሮሞ ህዝብ በኢትዮጵያዊነቱ ላይ ተደራድሮ አያዉቅም::የትግራይም ህዝብ በኢትዮጵያዊነቱ ላይ ተደራድሮ አያዉቅም:: ወያኔ እና ኦነግ/ኦህዴድ ግን በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ የስነልቦና ቀዉስ ዉስጥ የተመሰጉ የህሊና ህመምተኞች ናቸዉ::አንዴ ኢትዮጵያዊ ላለመሆን ሲራገሙ::ሌላ ጊዜ ኢትዮጵያዊ ለመሆን ሲዉተረተሩ የሚገኙ አሳዛኝ ፍጡሮች ናቸዉ::ወያኔ የትግራይን ህዝብ አይወክልም::ኦነግ/ኦህዴድም የኦሮሞን ህዝብ አይወክልም::ወያኔ እና ኦነግ/ኦህዴድ የሚወክሉት በራሳቸዉ የጥላቻ ፕሮፖጋንዳ የተቀረጸዉን የስነልቦና ቀዉስ የማንነት ቀዉስ ዉስጥ የተመሰጉ ግራ የተጋቡ የፖለቲካ ነጋዴዎችን ነዉ::

Source: Link to the Post

Leave a Reply