የትግራይ ልዩ ኃይልና ለህወሃት እኩይ ዓላማ ማስፈጸሚያ ከመሆን ይልቅ እጁን ለመከላከያ ሰራዊት በመስጠት ራሱንና ሕዝቡን እንዲያድን የተሰጠው የ3 ቀን የጊዜ ገደብ ዛሬ መጠናቀቁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገልፀዋል።
በዚህ ጥሪ የተጠቀሙ የትግራይ ልዩ ኃይልና ሚሊሺያ አባላት፣ ለወሰዱት ኃላፊነት የተሞላው ሕዝባቸውን የማዳን ውሳኔ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አመስግነው።
አሁን ግን የተሰጠው የጊዜ ገደብ ስለተጠናቀቀ በቀጣይ ቀናት የመጨረሻው ሕግ የማስከበር ወሳኝ ተግባር እንደሚከናወን አስታውቀዋል።
ህዳር 8/2013
Source: Link to the Post