የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ አመራሮች በጅማ ከተማ ከሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ጋር ተወያዩ

የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ አመራሮች በጅማ ከተማ ከሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 11፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ አመራሮች በጅማ ከተማ ከሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ጋር መከሩ።

የህወሓት ጁንታ የትግራይንና የኢትዮጵያን ህዝብ በድሏል ብለዋል የውይይቱ ተሳታፊዎች።

ቡድኑ ሀገር ለማፍረስ ላይ ታች ሲል ቀድሞ በቆፈረው ጉድጓድ ገብቷል ነው ያሉት።

በሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ የፈጸመው በደል ቡድኑ ሰው መሆኑን እንድንጠራጠር አድርጎናልም ብለዋል።

የትግራይ ህዝብ ከሌሎቸ ወንድም እና እህት የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር የሀገሪቷን ህልውና ሲጠብቅ መቆየቱን ገልፀዋል።

የፓርቲው ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ነቢዩ ስሁል የትግራይ ህዝብ በህወሓት ጁንታ ተነግዶበታል፤ ተጠቃሚ አልነበረም ብለዋል።

ቡድኑ ለፓርቲው አባላት ቤተሰብ እንጂ ለህዝብ ጥቅም የቆመ እንዳልነበር አንስተዋል።

የፓርቲው ሌላኛው የስራ ሀላፊ አቶ ሀጎስ ወለወደኪዳን በበኩላቸው ፓርቲያቸው በሀገሪቷ ውስጥ ካሉ የክልሉ ተወላጆች ጋር አመርቂ ውይይት እያደረገ እንዳለ ገልፀዋል።

ህወሓት እና የትግራይ ህዝብ አንድ እንዳልሆኑም ህዝቡ በህግ ማስከበር ወቅት አቋሙን አሳይቷል ብለዋል።

The post የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ አመራሮች በጅማ ከተማ ከሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ጋር ተወያዩ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply