የትግራይ ተቃዋሚዎች ህወሓት ብቸኛው ተደራዳሪ መሆን አይገባውም አሉ

በትግራይ ጉዳይ የሚደረግ ማንኛውም ውይይት ህወሓት ብቻውን ሊፈፅመው አይገባም ሲሉ ሦስት የትግራይ ፓርቲዎች ባወጡት መግለጫ አስታወቁ።

ሳልሳይ ወያነ ትግራይ፣ ባይቶና እንዲሁም ውድብ ናፅነት ትግራይ የተባሉ ሦስት የክልሉ ፓርቲዎች ባወጡት የፅሑፍ መግለጫ የዓለም ማኅበረሰብ ጦርነቱ በሰላማዊ መንገድ እንዲቋጭ የሚያደርጉት ጥረት እንደሚያደንቁ ገልጸዋል።

ፓርቲዎቹ በሰላማዊ መንገድ ቀውሱ መፈታት እንዳለበት አቋማቸው መሆኑ ገልፀው ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ በትግራይ ላይ የአውሮፕላን ጥቃት እንዲቆም ሰብዓዊ ድጋፍ ያለገደብ እንዲገባና በጦርነቱ እጃቸው እያስገቡ ናቸው ያሏቸውን ሃገራት እንዲቆጠቡ በማድረግ ተግባራዊ እርምጃ ሊወሰድ ይገባል ብለዋል።

ትግራይ አስመልክቶ በሚደረግ ውይይት ህወሓት ብቻውን ሊፈፅመው አይገባም፣ ዘላቂ ሰላም የሚመጣው የክልሉ ሁሉንም ፓርቲዎች ባካተተና ሁሉም የትግራይ ኃይሎች ባሳተፈ መልኩ ሊፈፀም ይገባል በማለት ገልጸዋል።

ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብም ይህንን ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ ነው የሰላም ሂደቶች መፈፀም የሚገባው ብለዋል ፓርቲዎቹ።

ዘገባውን ያደረሰን በመቀሌ የሚገኘው ሪፖተራችን ሙሉጌታ አጽብሃ ነው፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply