የትግራይ ተቃዋሚ ፖርቲዎች ህወሃት የትግራይ ህዝብ ብቸኛው ወካይ ሆኖ በድርድሩ እንዳይቀርብ ጠየቁ

ይህን ያሉት ሳልሳዊ ወያነ፣ ነፃነት ትግራይ እና ባይቶና ናቸው

ሰኞ ሰኔ 20 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የትግራይ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከፌዴራል መንግስቱ ጋር እንደሚደረግ በሚታሰበው ድርድር ህወሃት የትግራይ ህዝብ ወካይ ሆኖ በድርድሩ እንዳይቀርብ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በፃፉት ደብዳቤ ጠይቀዋል፡፡

ይህንን ጥያቄ ያቀረቡት ሳልሳዊ ወያነ፣ ነፃነት ትግራይ እና ባይቶና የተባሉት ፓርቲዎች ሲሆኑ፤ ፓርቲዎቹ ይደረጋል ተብሎ በሚጠበቀው ድርድር ህወሃት የትግራይን ሕዝብ እንደማይወክል አሳስበዋል።

ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ግጭቱ በሰላም እንዲፈታ እያደረገ ያለው ጥረት የሚደነቅ ነው ያሉት ፓርቲዎቹ፤ ነገርግን ህወሃት የትግራይ ህዝብ ብቸኛ ተወካይ እንዳልሆነ ሊታወቅ ይገባል ብለዋል።

ፓርቲዎቹ ህወሃት የትግራይ ሕዝብ ወካይ ሆኖ የቀረበበትን መንገድን እንደማይቀበሉት ነው ያስታወቁት።

ይካሄዳል ተብሎ በሚጠበቀው ድርድር ህወሃት የትግራይን ህዝብ ጥቅም ያስከብራል ብለው እንደማያምኑም ፓርቲዎቹ በደብዳቤያቸው አስታውቀዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply