የትግራይ ተፈናቃዮችን በአፋጣኝ ወደ ቀዬአቸው ለመመለስ እንደሚሠሩ ፕሬዝዳንቱ አስታወቁ

https://gdb.voanews.com/01000000-0aff-0242-02e4-08db58ad47cd_tv_w800_h450.jpg

በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ምክንያት፣ ከትግራይ ክልል ልዩ ልዩ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ሰዎች ወደ ቀዬአቸው ለመመለስ ጠየቁ።በዛሬው ዕለት፣ ተፈናቃዮቹን ወክለው፣ ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ጋራ ውይይት ያደረጉ ተፈናቃዮች፣ ወደ ቀዬአቸው ለመመለስ ተደጋጋሚ ጥያቄ ማቅረባቸውን አውስተው፣አፋጣኝ ውሳኔ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

ከክልሉ የማኅበረሰብ ተወካዮች ጋራ ውይይት ያደረጉት አቶ ጌታቸው፣ ከፌዴራሉ መንግሥት ጋራ በመተባበር ተፈናቃዮችን ወደ ቀዬአቸው የመመለሱን ሥራ እንደሚያስፈጽሙ ተናግረዋል፡፡

የተጠያቂነት እና በክልሉ ውስጥ አሉ የተባሉ የጸጥታ ስጋቶች፣ ከተሳታፊዎቹ በኩል መነሣታቸውን፣ የአሜሪካ ድምፅ ሰምቷል። ከማኅበረሰቡ ጋራ የተደረገው ይኸው ውይይት፣ ለብዙኃን መገናኛዎች ዝግ ኾኖ የተካሔደ ነበር።

በሌላ ዜና፣ የ42 ሀገራት ኤምባሲዎች ወታደራዊ አታሼዎች፣ የሰላም ስምምነቱ ትግበራ ሒደት ያለበትን ኹኔታ በመጎብኘት ላይ ናቸው።

ሙሉጌታ ሙሉጌታ ኣጽብሓ የዘገባዎቹን ዝርዝር ይዟል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply