የትግራይ ክልል ኢንዱስትሪ ቢሮ በዘጠኝ ወራት ጊዜ ዉስጥ ከ9መቶሺህ ዩሮ በላይ ገቢ ማግኘቱን ገለጸ፡፡

የክልሉ ኢንዱስትሪ ቢሮ ወደ ዉጪ ከተላከ የጨርቃጨርቅ ምርት 9መቶ8ሺህ 9መቶ85 ዩሮ ማግኘቱን ሰምተናል፡፡

በተጨማሪም 277 ሺህ ዶላር ከኬሚካል ግብዓቶች መገኘቱም ተገልጿል።

በጨርቃጨርቅ 7.9 ቶን እና በኬሚካል ደግሞ 4.6 ቶን በአጠቃላይ 12.5 ቶን ወደ ዉጪ መላኩን የነገሩን የቢሮዉ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ዳዊት ገ/ጻድቅ ናቸዉ፡፡

ኤክስፖርት የሚያደርጉት ሁለት ከፍተኛ የጨርቃጨርቅ አምራች ኢንተርፕራይዞች መኖራቸውንም ገልፀዋል።

በሌላ በኩል በአገር ውስጥ ተኪ ምርት በማምረት ጨርቃጨርቅ 5መቶ40ሺህ ፤አግሮ ፕሮሰሲንግ 1ሚሊየን 5መቶሺህ እንዲሁም ብረታብረት ከ1ሚሊየን ዶላር በላይ ማዳን መቻሉ ተገልጿል።

በአጠቃላይ 3ሚሊየን 9መቶ11ሺህ6መቶ ዶላር ለማዳን ተችሏል ሲሉ ተናግረዋል ፡፡

በዚህም 24 ኢንተርፕራይዞች ተኪ ምርት የሚያመርቱ ሲሆን 5 አነስተኛ፣ 9 መካከለኛ እና 10 ከፍተኛ ኢንተርፕራይዞች መሆናቸውን ገልጸዋል።

እስከዳር ግርማ

ግንቦት 23 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply