የትግራይ ክልል የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ከፌደራሉ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ጋር ያለውን ግንኙነት አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ፡፡የትግራይ ክልል የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤ…

የትግራይ ክልል የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ከፌደራሉ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ጋር ያለውን ግንኙነት አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ፡፡

የትግራይ ክልል የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ትላንት ካደረገው አስቸኳይ ጉባኤ በኃላ ባወጣው መግለጫ ፤ ” የፌደራል እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ጥር 7/2016 ዓ.ም በላከው ደብዳቤ ጦርነቱን ባለመቃወሙና ባለማውገዙ ስህተት መሆኑን አምኖ ይቅርታ ጠይቋል ” ብሏል።

ምክር ቤቱ በጉባኤው የተገኙት የመላ ትግራይ የሙስሊም ማህበረሰብ ተወካይ አባላት ሰፊ ውይይት በማድረግ የቀረበውን የይቅርታ ደብዳቤ በሙሉ ድምፅ መቀበላቸውን አሳውቋል።

ም/ቤቱ ይቅርታውን እንዲቀበል ካስቻሉት ዋና ምክንያቶችም ዘርዝሯል።

-የትግራይ ሙስሊሞች ሃይማኖታዊ ግዴታ የሆነው የሀጅና ዑምራን እና ልሎች ሃይማኖታዊ አገልግሎቶች በፌደራል እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ብቻ ስለሚሰጡ፤

-የትግራይ አስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት የሀጅና ዑምራን ሃይማኖታዊ አገልግሎት በራሴ መንገድ አካሂዳለው ካለ የግድ ከኤምባሲዎችና ከቆንስላዎች ግንኙነት ማድረግ ስለሚጠበቅበት ፤ ይህ ስልጣን ደግሞ ለፌደራል እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ ቤት ብቻ የተፈቀደ በመሆኑ፤

በዚህንና ሌሎች የትግራይ የሙስሊም ማህበረሰብ መብቶች የሚያስክብሩ ጉዳዮች ግምት ውስጥ በማስገባት የቀረበው የይቅርታ ደብዳቤ በምክር ቤት አባላቶች በሙሉ ድምፅ ተቀባይነት ማግኘቱን ይፋ አድርጓል።

ጥር 17 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Source: Link to the Post

Leave a Reply