የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ነጻ በሆኑ አካባቢዎች መዋቅሩን እንደሚያደራጅ ገለጸ፡፡የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከህወሓት ቡድን ነጻ በሆኑ አካባቢዎች መዋቅሩን እንደሚያደራጅ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ዋና ስራአስፈጻሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ ገልፀዋል።ዋና ስራ አስፈጻሚው በሰጡት መግለጫ፤ ዋና ስራ አስፈጻሚው የፕሬዚዳንቱን ስራ ስለሚሰራ ክልሉ ሙሉ ለሙሉ ነጻ ሲወጣ መንግስታዊ ስራውን ተክቶ እንደሚሰራ ተናግረዋል።
በዚህም መሰረት የክልሉን ካቢኔ እንደሚያደራጅና የዞን አስተዳዳሪዎችን እንደሚሾም ገልጸው፤ የወረዳና የቀበሌ ምክር ቤቶች ባሉበት እንዲቀጥሉ የሚደረግ መሆኑን አመልክተዋል።ስራ አስፈጻሚውን አካል እንደሚመራ፣ እንደሚያስተባብር እንዲሁም የክልሉን ዕቅድና በጀት እንደሚያጸድቅ ጠቁመዋል።
ህዳር 8/2013
Source: Link to the Post