የትግራይ ክልል ግዚያዊ አስተዳደር ለሕገ-መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ምላሽ እንዲሰጥ ትዕዛዝ ተሰጠው፡፡ጊዜያዊ መስተደዳድሩ በ ደንብ ቁጥር 4/2016 ከጥቅምት 24 2013 እስከ ጥቅምት…

የትግራይ ክልል ግዚያዊ አስተዳደር ለሕገ-መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ምላሽ እንዲሰጥ ትዕዛዝ ተሰጠው፡፡

ጊዜያዊ መስተደዳድሩ በ ደንብ ቁጥር 4/2016 ከጥቅምት 24 2013 እስከ ጥቅምት 23 2015 ዓ.ም ባለው ሁለት ዓመት ውስጥ ማንኛውም አካል ደሞዝ መጠየቅ አይቻልም ማለቱን ተከትሎ በጉዳዩ ላይ ምላሽ እንዲሰጥ ተጠይቋል።

በደንብ ላይ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ምላሽ እንዲሰጥበት የሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ትእዛዝ መሰጠቱን ጣብያችን ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል፡፡

የቅድሚያ ለሰብዓዊ መብቶች ምክትል ዳይሬክተር የሆኑት አቶ መብሪህ ብርሃኔ ከጣብያችን ጋር በነበራቸው ቆይታ ይህ መሸጋገሪያ ደንብ አራት የህገ-መንግስቱ መሰረታዊ ሀሳቦች ጋር የሚቃረን ነው ብለዋል፡፡

ይህንን ደንብ በተመለከተ ድርጅቱ ለህገ-መንግስታዊ አጣሪ ጉባኤ አቤቱታ ማቅረቡን የገለፁት ዳይሬክተሩ ጉባኤውም የክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ምላሽ እንዲሰጥበት ትዕዛዝ መስጠቱን ተናግረዋል፡፡

ግዚያዊ አስተዳደሩ በዋነኝነት የመጀመሪያው ከጥቅምት 24 2013 እስከ ጥቅምት 23 2015 ዓ.ም ባለው ሁለት ዓመት ውስጥ ማንኛውም አካል ደሞዝ መጠየቅ አይችልም ሲል በአዲሱ መሸጋገሪያ ደንብ ላይ አሰፍሮ ይገኛል፡፡

ይህ ደግሞ እንደየሁኔታው እየታየ በፍርድ ቤት የሚወሰን እንጂ የዜጎች ን ፍትህ የማግኘት መብት መገደብ የለበትም በሚል አቋም መሆኑ ድርጅቱ ገልፃል፡፡

ስለሆነም በትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ከህዳር 28/03/2016 ዓ/ም ጀምሮ ተፈፃሚ እንዲሆን የወጣው ደንብ ቁጥር 4/2016 የህገ መንግሰቱን መሠረታዊ ሀሳቦች የሚጣረስ በመሆኑ አቤቱታውን ቅድሚያ ለሰብዓዊ መብት አቅርቧል፡፡

የህገ-መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤም የቀረበለትን አቤቱታ ከተመለከተ በኃላ የትግራይ ክልል ግዚያዊ አስተዳደር ምላሽ እንዲሰጥበት ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡

በአቤል ደጀኔ

ግንቦት 14 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply