የትግራይ ወራሪ ሃይል በሁመራ ተደጋጋሚ ትንኮሳ እያደረገ ነው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሀምሌ 15 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የትግራይ ወራሪ ሃይል በጣረሞት ውስጥ…

የትግራይ ወራሪ ሃይል በሁመራ ተደጋጋሚ ትንኮሳ እያደረገ ነው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሀምሌ 15 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የትግራይ ወራሪ ሃይል በጣረሞት ውስጥ ሆኖም በሁመራ በኩል ተደጋጋሚ ትንኮሳዎች እያደረገ ስለመሆኑ ተገልጧል። ከሰሞኑ ባደረጋቸው ትንኮሳዎች በርካታ አባሎቹ ተደምስሰዋል ተብሏል። የአማራ መስተዳድር ወሰን ውስጥ በመግባት ከማይካድራ በአምስት ኪሎ ሜትር ርቀት ልጉዲ ላይ ካምፕ መስርቶ ነው ጥቃት እየሰነዘረ የሚገኘው። የተኩስ ልውውጡ ከሰሞኑ ሲደረግ የሰነበተ ሲሆን ትናንት ረቡዕ ሀምሌ 13 ቀን 2014 ዓ.ም. ከዲማ እስከ ረዲም የተኩስ ልውውጥ መደረጉ ተገልጧል። በተኩሱም በጣረሞት ላይ የሚገኘው የትግራይ ወራሪ ሃይል ወታደሮች በከፍተኛ ደረጃ የተደመሰሱ ሲሆን ከቀናት በፊት አንድ ፋኖ ተሰውቷል። በአካባቢው መቻ ቀበሌ ላይ የነበሩ የቀን ሠራተኞችን አግተው የወሰዱ ቢሆንም በተደረገው ውጊያ ማስመለስ ተችሏል። “በአካባቢው የሚገኘው የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የአማራ ልዩ ሃይል እየተከላከለ ቢሆንም ወያኔዎች ልጉዲን ለቀው ሊሸሹ ሲሉ ግን ይተዋቸዋል። ለምን እስከ መጨረሻው ማጥቃት እንዳልተፈለገ አይገባኝም” ብለዋል የመረጃ ምንጮች። ፋኖዎች ወደ ፊት ገስግሰው ሊያስለቅቁ ሲሉ በመንግሥት ሃይሎች እየተመለሱ መሆኑን ገልፀዋል። ዜናው_የጋዜጠኛ ጌጥዬ ያለው ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply