የትግራይ ግዜያዊ አስተዳደር ወደ ተሳሳተ መንገድ እየሄደ መሆኑን ዶ/ር ሲሳይ መንግስቴ ተናገሩ           አሻራ ሚዲያ     ጥር፡-14/05/13/ዓ.ም ባህር ዳ…

የትግራይ ግዜያዊ አስተዳደር ወደ ተሳሳተ መንገድ እየሄደ መሆኑን ዶ/ር ሲሳይ መንግስቴ ተናገሩ አሻራ ሚዲያ ጥር፡-14/05/13/ዓ.ም ባህር ዳ…

የትግራይ ግዜያዊ አስተዳደር ወደ ተሳሳተ መንገድ እየሄደ መሆኑን ዶ/ር ሲሳይ መንግስቴ ተናገሩ አሻራ ሚዲያ ጥር፡-14/05/13/ዓ.ም ባህር ዳር የቀድሞው ህውሀት ወደ ስልጣን ከመጣ ጀምሮ ከመንበሩ ስልጣኑ እስከተወገደበትድረስ በሀገራችን በተለያዩ ክፍሎች በርካታ ኢ -ሰብአዊ ድርጊቶችን ሲፈጽምና ሲያስፈጽም መቆየቱ ይታወቃል፡፡ … ንጹሀንን በማንነታቸውና በቋንቋቸው እየለየ ሲያሳድድና ሲያፈናቅል እንዲሁም ህይወታቸው እንዲያልፍ በማድረግ ከፍተኛ የሆነ ሚና መጫወቱም ይታወሳል፡፡ ለዚህ ማሳያ ደግሞ የወልቃይትና የራያ አማራዎች ተጠቃሾች ናቸው፡፡ ስለሆነም ህግን መሰረት ባላደረገ መልኩ ማንነትንና ቋንቋን በመደፍጠጥ የወልቃይትንና የራያን ህዝብ ያለፍላጎታቸው ወደ ትግራይ በማጠቃለል ከፍተኛ የሆነ ግፍ ሲፈጽም ቆይቷል፡፡ ይሁን እንጅ የቀድሞው ህውሀት በከፈተው ጦርነት ምክንያተ መንግስት ህግን ለማስከበር ባደረገው ዘመቻ በጉልበት ወደ ትግራይ የተካለሉ አካባቢዎች እንዲመለሱ እንዲሁም በአካባቢው የሚገኙ ነዋሪዎችም ነጻ እንዲወጡ ተደርጓል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ከቀድሞው ህውሀት ነጻ የወጡትን ህዝቦችና አካባቢዎች አስመልክቶ የትግራይ ግዜያዊ አስተዳደር የሚሰጣቸው መግለጫዎች የተሳሳቱ መሆናቸውን ዶ/ር ሲሳይ መንግስቴ ተናግረዋል፡፡ በትግራይ የተቋቋመው ግዜያዊ አስተዳደር ከህውሀት ነጻ የወጡትን ራያንና ወልቃይትን የትግናይ ናቸው ብሎ ካሰበ አሁንም የትህነግን ዓላማ ለማስቀጠል መንደርደሪያ መሆኑን ማሳያ ናቸው ብለዋል፡፡ ህግን ለማስከበር በተደረገው ዘመቻ የአማራ ልዩ ሀይል ማንነታቸውን የተነጠቁ ህዝቦችን ነጻ አውጥቷል ያሉት ዶክተሩ አሁንም ልዩ ሀይሉ በአካባቢው እንዲቆይ ትዕዛዝ ተሰጥቷል ሲሉም ተናግረዋል፡፡ ስለሆነም የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የአማራ ከልል ልዩ ሀይል ከቦታው እንዲወጣ ከፌደራል መንግስት ጋር ውይይት ተደርጓል ያሉት ፍጹም የተሳሳተና ሊሆን የማይችል መሆኑን ዶ/ር ሲሳይ መንግስቴ ጠቁመዋል፡፡ ዘጋቢ፡-ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply