
በኢትዮጵያ መንግሥት እና በትግራይ ኃይሎች መካከል የሚደረገው ንግግር በነሐሴ ወር ሊጀመር ይችላል ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ አንድ የአሜሪካ ከፍተኛ ባለሥልጣን መናገራቸውን የፈረንሳይ ዜና ወኪል (ኤኤፍፒ) ዘገበ። ሞሊ ፊ በሰሜን ኢትዮጵያ የሚካሄደውን ጦርነት በሽምግልና ለመፍታት ቁልፍ ሚና አላት ባሏት ኬንያ ውስጥ የሚካሄደውን ምርጫ ተከትሎ ድርድሩ እንደሚጀመር ጥንቃቄ የተሞላበትን ተስፋቸውን ለአገራቸው ምክር ቤት ኮሚቴ መናገራቸውን ኤኤፍፒ አመልክቷል።
Source: Link to the Post