
ባለፈው ሳምንት የመጨረሻ ቀናት የኤርትራ ጦር በሽራሮ ከተማ ላይ በከፈተው ጥቃት አንዲት የ14 ዓመት ታዳጊ መገደሏን እና 18 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘገበ። ሮይተርስ ከሰብዓዊ ድርጅት ተቋማት የተገኘ መረጃ የሰፈረበት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰነድን ተመልክቻለሁ ብሎ ባወጣው ዘገባ፣ የኤርትራ ጦር ቢያንስ 23 ጊዜ ወደ ሽራሮ ከባድ መሳሪያ ተኩሷል ብሏል።
Source: Link to the Post