የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አስመራ ገቡ

በቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ የተመራ የልኡካን ቡድን ኤርትራን ለመጎብኘት በዛሬው ዕለት አስመራ መግባቱና ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂም ጋር ተገናኝቶ መነጋገሩ ተነገረ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዋንግ ዪ ከቻይናው መሪ ፕሬዚዳንት ዢ ጂፒንግ የተላከ መልዕክት ለኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ማድረሳቸው የተመለከተ ሲሆን ቻይናና ኤርትራ የጋራ ግንኙነታቸውን ለማጠንከር መስማምታቸው ተገልጿል፡፡ 

የኤርትራው መሪ ቻይናን እንዲጎበኙ ከቻይናው ፕሬዚዳንት ጥሪ የተደረገላቸው መሆኑም ከስፍራው በደረሰን ዘገባ ተመልክቷል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply