የቻይናው ፕሬዝደንት ሺ ዢንፒንግ እና የሩሲያው አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን አሜሪካ በየሀገሮቻቸው የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ እየገባች ነው ሲሉ መክሰሳቸውን ክሬምሊን አስታወቀ። ሁለቱ ፕሬዝደንቶች አሜሪ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/A8v-AUGwZ-Fh9sI5q3Frt_9zFLMKxmBg9BBTRxDJJU11CM9AUbgjn2uGXG9aRALLFI3QC1fWZV_cKFEsG18mxIHi-cd42n2NnIJJGO_RptQs62mlmwgznLckhM1ekKW-wm0ymCPyH9u8equVG_xHqb93pBZXvBCWjKmD75y2AS0JJvef1U8SExba2OW0Ruv9_rD8a9xS9T06Y7RSBlKkBSKZH3YwPRbBuOdadaGMlWvHrdfXssI4cRZVQmDznh8eXhbY2Uj8P4_VwaQZTnl6sUowyUXgNBJc0ExdRsm1bl__e0FCo12rj6USx7_k0DINS3EHSNnUIC0VCcTEaavQAg.jpg

የቻይናው ፕሬዝደንት ሺ ዢንፒንግ እና የሩሲያው አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን አሜሪካ በየሀገሮቻቸው የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ እየገባች ነው ሲሉ መክሰሳቸውን ክሬምሊን አስታወቀ።

ሁለቱ ፕሬዝደንቶች አሜሪካ ላይ ክሱን የሰነዘሩት ዛሬ ሐሙስ በስልክ በተነጋገሩበት ወቅት ነው።

ለአንድ ሰዓት የረዘመ በተባለው የስልክ ንግግር ሺ እና ፑቲን “የአሜሪካን በሌሎች ሀገሮች የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ የመግባት ፖሊሲ” እንዳወገዙ የሩሲያ ፕሬዝደንት ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

ምዕራቡ ዓለም ቻይና እና ሩሲያ ዓለም አቀፍ ተጽዕኗቸውን እያጠናከሩ ናቸው የሚል ሥጋት አለው። በተለይ ባለፉት ሁለት ዓመታት ቻይና እና ሩሲያ በንግድ እና በመከላከያ ዘርፎች ግንኙነቶቻቸውን እያሳደጉ ሲሔዱ ታይቷል።

ሩሲያ ዩክሬንን ከመውረሯ በፊት ቤጂንግ እና ሞስኮ ወዳጅነታቸው “ገደብ የለሽ” እንደሆነ አውጀው ነበር። ከዩክሬን ጦርነት ከተቀሰቀሰም በኋላ ቻይና ለሩሲያ ታደላለች እየተባለች ትወነጀላለች።

በዛሬው የስልክ ንግግር ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን “ለአንድ ቻይና ፖሊሲ” ያላቸውን ቁርጠኝንት በድጋሚ እንዳረጋገጡ ጽህፈት ቤታቸው አስታውቋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጥር 30 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos
Facebook  https://www.facebook.com/onelovebroadcast
Website https://ethiofm107.com/

Source: Link to the Post

Leave a Reply