በኢትዮጵያ ኢንድስትሪ ዞኖች፣ የቻይና የኮንስትራክሽን ኩብንያዎችና የወያኔ አንደኛ ደረጃ ኮንትራክተሮች የተዘረፈ፣ ያልተጠና የሾዶች የ10 ቢሊዮን ዶላር የብድር ግንባታ ወጪ በዋና ኦዲተር ምርመራ ይደረግባቸው!!!
በኢትዮጵያ የ2010 ዓ/ም በጀት እቅድ መሠረት የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ እቅድ 997 ሚሊዮን ዶላር የነበረ ሲሆን የእቅዱ አፈፃፀም ግን 487.5 ሚሊዮን ዶላር ማለትም 57.8 በመቶ ሆኖል ከዚህ ውስጥ የኢንዱስትሪ ዞኖች ድርሻ አናሳ በመሆኑ አልተገለፀም፡፡ ሁላችሁም ከምርኮኛ ፖለቲከኝነታችሁ ተላቅቃችሁ የኢኮኖሚውን ብዝበዛና ዘረፋ በሕብርት ለማስቆም እስካልተባበርን የሃገሪቱ ኢኮኖሚ አያንሰራራም፡፡ የኢንዱስትሪ ዞኖች ሼዶች ግንባታ ወጪ ቆሞ የገቢ ንግድ የሚተኩ ኢንዱስትሪዎች (Import Substitution Industrialization (ISI) መተካት ይኖርባቸዋል እንላለን፡፡ ከውጪ የሚገቡ የፍጆታ እቃዎችን በማቆምና በሃገር ውስጥ አምርቶ በመተካት የውጭ ምንዛሪ ማዳን ይቻላል፡፡ ለምሳሌ በሰሊጥ ምርታችን የዘይት ፋብሪካ በማቆቆም ምርቱን በሃገር ውስጥ በማከፋፈል የውጭ ምንዛሪ ማዳንና ለወጣቶች የሥራ እድል መፍጠር ይቻላል፡፡
የኢንደስትሪ ፓርክ ግንባታ የፋብሪካዎች ሼዶች ሥራ በብዙ ሄክታር መሬት ላይ የሚደረግ ሲሆን የግንባታው ዲዛይንና የተቀራጭ ኮንትራክተር መረጣ ከቻይናዎቹ ኮንስትራክሽን ካንፓኒዎች አንዱን በማድረግና ከቻይና ኤግዚም ባንክ ብድር በማመቻቸት ተቆራጩ ሥራውን ያከናውናል፡፡ በልዩ ኢንደስትሪ ዞኖች ለመመሥረት በጥናት ላይ የሚገኘው የቻይና የልማት ዞኖች ማሕበር (“CADZ”) መሰረት አራት የቻይና ኮንስትራክሽን ኩባንዎች CCCC፣ CCECC፣ CGCOC፣ እና CREC” ያካትታሉ፡፡ እነዚህ የቻይና ኩብንያዎች በሃገራቸው ያረጁ ያፈጁ ፋብሪካዎችን ነቀላና ተከላ በማድረግ በኢግዚም ባንክ ብድር በማመቻቸት በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ሾዶች ያለ አንዳች ጥናት ይገነባሉ፡፡ የቻይና ኩብንያዎች በመሰረተ ልማት፣ በግብርና ልማት፣ በማዕድን ፍለጋ፣ በፋይናንስ፣ በባንክ፣ በሳይንስና ቴክኖሎጅ፣ በኮንስትራክሽንና በማኑ-ፋክቸሪንግ ዘርፎች ላይ በመሳተፍ ላይ የይገኛሉ፡፡ በኢንዱስትሪያል ፓርኮች ግንባታ ስም ፣ የቻይና ኮንስትራክሽን ካንፓኒዎች ከፍተኛውን ድርሻ ሲቀራመቱ የህወሓት የጦር አበጋዞች ሽርካ የሆኑ የኮንስትራክሽን ካንፓኒዎች ቀሪውን ሥራ የተቀራመቱ የንግድ ካንፓኒዎች መሃከል ናቸው፡፡ የኢንደስትሪ ፓርኮች ሼዶች ግንባታ የሌብነትና ሙስና ታሪክ ገና ይወጣል፡፡
አቶ ተክለብርሃን አምባዬ፣ Teklebrehan Ambaye Construction Plc (TACON)፣ የኢንዱስትሪያል ፓርክ ሁለት ትልልቅ ፋብሪካዎች ሼድ በ80 ሚሊዮን ብር የግንባታ ወጪ ሠርቶል፣ እንዲሁም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ወለጋ ዮኒቨርሲቲ ወዘተ ባለፈው 27 አመታት ብዙ ሥራ በወያኔ ተሠጥቶት ቢሊየነር ሆነ፡፡ Teklebrehan Ambaye Construction Plc (TACON), Two of the largest factories, that cost around 80 million Br, are to be constructed by Teklebrehan Ambaye Construction Company, which is recently awarded for the construction of the tallest branch office of Commercial Bank of Ethiopia (CBE) on Equatorial Guinea Street, and AMB Construction Plc established in 2006, and currently constructing Wollega University. በተመሳሳይ ተ/ብርሃን አምባዬ ሪል እስቴት በድምሩ 100,000 ካሬ ሜትር የቦታ ስፋት ከመንግስት ወስዶ መሬት በመሸጥ ጭምር የተጠቀመ ድርጅት ነው፡፡ ዘረፋው የተከናወነው በመንግስትና በባለ ሃብቱ ነው፡፡ በአቶ ተክለብርሃን አምባዬ ኮንስትራክሽን ወያኔ ኢህአዴግ ስልጣን ላይ ከወጣ በሆላ የተመሠረተ ድርጅት ነው፡፡ በአሁኑ ግዜ ከአምስት ቢሊዩን ብር በላይ በሚያወጡ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ግንባታ እየሰራ የሚገኝ ድርጅት ነው፡፡ ከነዚህ ፕሮጀክቶች ውስጥ በሲኤምሲ አካባቢ የሚገነባው የሚኒስትሮች መኖሪያ ቪላ ቤቶች፣የ40/60 የኮንዶሚኒየም ቤቶች ግንባታ፣የአፍሪካ ኢንሹራንስ ባለ 11 ፎቅ ሕንፃ በ143 ሚሊዩን ብር የግንባታ ወጭ፣ለኢትዩጵያ ንግድ ባንክ ልደታ ቅርንጫፍ ግንባታ፣በትግራይ ክልል የሚገነባ ብሔራዊ ስታዲየም፣በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የሚገነባ የስፖርት አካዳሚ፣የያዩ ማዳበሪያ ፋብሪካ፣ለከተማ ልማት፣ለቤቶችና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የሚያከናውናቸው ፕሮጀክቶች ከሚጠቀሱት ሥራዎች መኃል ይገኛሉ፡፡ ቦሌ ለሚ ኢንደስትሪያል ዞን በአዲስ አበባ ከተማ በቦሌ ለሚ ለደቡብ ኮሪያ ኢንቨስተሮች የሚገነባው ኢንደስትሪያል ዞን 633 ሚሊዩን ብር የግንባታ ወጪ እንዳለው የኢንደስትሪ ሚኒስቴር ለ13 የአገር ውስጥ ኮንትራክተሮች ስራውን ሰጥተዋል፡፡ ፋብሪካዎቹ የሚገነቡት በ156 ሄክታር መሬት ላይ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ የደቡብ ኮሪያ ኢንቨስተሮች ስምንት ካንፓኒዎች በጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ኢንደስትሪያል ዘርፍ እንደሚሳተፉ ተገልፆል፡፡
ሳህለማርያም ኮንስትራክሽን የኢንዱስትሪያል ፓርክ ሦስት ትልልቅ ፋብሪካዎች ሼድ ሥራ በወያኔ ጀባ ተብሎታል፣ እያንዳንዳቸው ሼዶች 5 ሽህ ስኩየር ሜትር ስፋት አላቸው፡፡ Sahle Mariam Construction, grade one contractors are assigned to construct the three factory shades that rest on 5,000sqm each.
ኤኤምቢ ኮንስትራክሽን የኢንዱስትሪያል ፓርክ ሦስት ትልልቅ ፋብሪካዎች ሼድ ሥራ በወያኔ ጀባ ተብሎታል፣እያንዳንዳቸው ሼዶች 5 ሽህ ስኩየር ሜትር ስፋት አላቸው፡፡ AMB Construction, grade one contractors are assigned to construct the three factory shades that rest on 5,000sqm each.
ቲ ኤንቲ ኮንስትራክሽን የኢንዱስትሪያል ፓርክ ሦስት ትልልቅ ፋብሪካዎች ሼድ ሥራ በወያኔ ጀባ ተብሎታል፣እያንዳንዳቸው ሼዶች 5 ሽህ ስኩየር ሜትር ስፋት አላቸው፡፡ TNT Construction and grade one contractors are assigned to construct the three factory shades that rest on 5,000sqm each.
ሲጂሲኦሲ ኢትዮጵያ የቻይና ካንፓኒ የኢንዱስትሪያል ፓርክ የውስጥ ለውስጥ የ12 ኪሎ ሜትር መንገድ ሥራ ይሰራል፡፡ The China based CGCOC Ethiopia Ltd. Chinese Company is awarded for a 12km of alleyway road construction inside the industrial zone.
ራማ ኮንስትራክሽን የኢንዱስትሪያል ፓርክ አራት ቢሮዎች ሥራ በወያኔ ጀባ ተብሎታል፣ Rama Construction Plc, Rama is assigned to construct the four offices blocks
ቀሪው ሃበር ኮንስትራክሽን፣ ዩናይትድ ኮንስትራክሽን፣ ፉፋ ኮንስትራክሽን፣ ካሱ ገብረፃዲቅ፣ አምሃ ስሜና ቀሻሞ ኮንስትራክሽን ከሦስት እስከ አምስት ኮንስትራክሽን የአጥር ማጠር፣አምስት ሎንጅ፣ ፖሊስ ስቴሽን፣ ስድስት የጥበቃ ቤቶችና መፀዳጃ ቤቶች የሆኑ የሁለት ሚሊዮን ብር ሥራ ሲሰጣቸው ኮንትራክተሮቹ የ20 ሚሊዮን ብር ሥራ የመስራት ፍቃድ እያላቸው ዝቅተኛ ሥራ ብቻ እንደሚሰጣቸው ቅሬታ አሰምተው ነበር፡፡ The remaining third to fifth grade contractors signed a contract to construct the fence, five lounges, police stations, six guard houses and six toilet and shower houses. These companies are Haber Construction Plc, United Construction Plc, Fufa Legesse Construction Plc, Kasu Gebretsadik Construction Plc, Amha Sime Construction Plc and Keshamo Construction Plc. However, some of these companies were not happy with the contract allotment arguing that they are made to construct below their capacity. “We did not expect a two million Birr contract while the MoUDC certified us for doing up to 20 million Br contract on a yearly basis,” Kasu Gebretsadik, managing director of Kasu Gebretsadic Construction Company, awarded to construct the guard houses, told Fortune.
የኢትዩጵያ ኢንደስትሪያል ዞኖች ልማት፣ የኢትዩጵያ ኢንደስትሪ ሚኒስትር ስር የተቆቆመው የኢትዩጵያ ኢንደስትሪያል ዞኖች ልማት ኮርፖሬሽን Ethiopian Industrial Zones Development Corporation (EIZDC) በፌዴራል ኤጀንሲ ስር ይተዳደራል፡፡ ኮርፖሬሽኑ፣ ቅድሚያ የተሰጣቸው የማኑ-ፋክቸሪንግ ኢንደስትሪ ዘርፎች ውስጥ ጨርቃ ጨርቅና አልባሳት፣ ቆዳና የቆዳ ውጤቶች፣ የስኮር ፋብሪካና የስካር ውጤቶች፣ ኬሚካል፣ ፋርማሲዩቲካልና አግሮ ፕሮሰሲንግ ላይ ኢንቨስትመንት ለሚያደርጉ የታክስና ቀረጥ የማንሳት ማበረታቻ በ769/2012 እኤአ በወጣው አዋጅ ለማድረግ ተደንግጎል፡፡ ሚኒስትር ቢሮ 5,130 ሄክታር መሬት ለኢንድስትሪ ዞኖችን ለማስፋፋት ቦታውን ተረክቦል፡፡‹‹In alignment with GTP goals to further develop medium and large scale industries, the government established the Ethiopian Industrial Zones Corporation under the Ministry of Industry in 2012 to oversee the construction and regulation of the zones.
INDUSTRIAL PARK PROJECTS
In and around | Operational | Size | Lots type |
Distance To Addis |
Distance To Djibouti |
Clusters |
Addis | ||||||
•Bole Lemi I | Operational | 156 Ha | Pre-built factories | 15 Km | 863 km | Apparel(Fully subscribed Parks |
•Bole Lemi II | 2016 | 186 Ha | Pre-built factories & Serviced land | 15 km | 863 Km | Textile & Apparel |
•Kilinto | 2016 | N/A | TBD | 15 Km | 863 Km | Pharmaceutical |
Outside Addis | ||||||
•Hawassa | 2015 | 300 Ha (phase1) |
Pre-built factories & Serviced land |
275 Km | 998 Km | Textile & Apparel (Fully subscribed Parks |
•Dire Dawa | 2016 | 1500Ha | TBD | 445 Km | 380 Km | Textile & Apparel, Food Processing, assembly |
•Kombolcha | 2017 | 700 | TBD | 363 Km | 480 Km | Textile & Apparel, Food Processing |
•Mekelle | 2017 | 1000 | TBD | 760 Km | 750 Km | Textile & Apparel, Food Processing, assembly |
• Adama | 2017 | 2000 | South East | 74Km | 789 km | Textile & Apparel, Food Processing |
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ሼድ መሥሪያ አስር ቢሊዮን ዶላር ማውጣት የሃገሪቱ ኢኮኖሚ በእዳ መዝፈቅ ስለሚሆን የዶክተር አብይ መንግሥት ምሁራኖችን ማስጠናት ይኖርባቸዋል እንላለን፡፡የኢንዱስትሪ ፓርኮች ሼድ ሠርቶ ለባህር ማዶ ኢንቨስተሮች መስጠት አዋጭ አይደለም፣ ከውሃ ማቆር ወደ ፋብሪካ ማቆር/ ባዶ የንብ ቀፎ ሰቅሎ ማር ቆረጣ እንዳይሆን እስካሁን የተሰሩት የወጪና ገቢ ጥናታዊ ዘገባ በባለሙያዎች ይጠና እንላለን፡፡ ከነዚህም ውስጥ፣
{1} የቦሌ ለሚ (አንድ) ኢንዱስትሪ ፓርክ፣ Bole Lemi I Industrial Park/በ2014 እኤአ የተጠናቀቀ ሲሆን፣ በመንግሥትና በዓለም ባንክ ብድር የተገነባ ሲሆን የ23 ሀገር በቀል የኮንስትራክሽን ካንፓኒዎች ተሳትፈውበታል፡፡ ከጁቡቲ ወደብ 860 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በመገኘቱ ተጨማሪ የትራነስፖርት ውጪ ስላለው በዓለም አቀፍ ንግድ ላይ በርካሽ ሽጦ ተወዳዳሪ መሆን አይቻለውም፡፡ Location : Located in the south eastern part of Addis Ababa ,4km away from Goro square/ Land area: 156 ha / Cluster: Apparel & Textiles and Leather and leather products (shoes) Labor: 10,000 / Shed & Land lease status : (10 sheds of of 5500 m2 and The remaining 10 sheds of 11,000 m2 each are already occupied for phase ) 1st phase: 156 Ha
{2} ቦሌ ለሚ (ሁለት) ኢንዱስትሪ ፓርክ፣ Bole Lemi II Industrial Park/ በመንግስት፣በአለም ባንክ ብድር የተሠራ ሲሆን በቻይና ካንፓኒ ሲጂሲኦሲ ኮንትራክተር የተገነባ ነበር፣ ከጁቡቲ ወደብ 860 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በመገኘቱ ተጨማሪ የትራነስፖርት ውጪ ስላለው በዓለም አቀፍ ንግድ ላይ በርካሽ ሽጦ ተወዳዳሪ መሆን አይቻለውም፡፡ ቦሌ ለሚ (ሁለት) ኢንዱስትሪ ፓርክ የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ኢንዱስትሪዎች ልማት የፕሮጀክቱ ወጪ 3.5 ቢሊዮን ብር ሥራ ተበርክቶለታል፣ አማካሪ ዳዋ የደቡብ ኮሪያ ኩባንያ፣ Proximity to port of Djibouti: 863 km / Cluster: Textile & Apparel/Land Area: 186 ha/
{3} ቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ፣Kilinto Industrial Park/በ2016 እኤአ ሲጠናቀቅ፣ በመንግስት፣በአለም ባንክና በቻይና መንግሥት ብድር የተሠራ ሲሆን በቻይና ካንፓኒ ሲቲሲኢ ኮንትራክተር የተገነባ ነበር፣ ከጁቡቲ ወደብ 860 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በመገኘቱ ተጨማሪ የትራነስፖርት ውጪ ስላለው በዓለም አቀፍ ንግድ ላይ በርካሽ ሽጦ ተወዳዳሪ መሆን አይቻለውም፡፡ በአቃቂ-ቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ የፋርማሲቲካል ኢንዱስትሪ፣ የመድኃኒትና የህክምና መሳሪያዎች የሚፈበረኩበት የፕሮጀክቱ ወጪ 5.5 ቢሊዮን ብር ሥራ ተበርክቶለታል፣ አማካሪ ዳዋ የደቡብ ኮሪያ ኩባንያ ሆኖል፣Proximity to port of Djibouti: 863 km /Proximity to Addis Ababa: 6km (access to high skill labour) /Cluster: Pharmaceuticals /Land Area: 337 ha/1st phase: 337 ha / የፋርማሲቲካል ኢንዱስትሪ፣ የጥሬ ዕቃ ግብዓቶች ኬሚካሎች 75 በመቶ በውጭ ምንዛሪ ከባህር ማዶ ተገዝተው የሚገቡ ናቸው፡፡
{4} የሃዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ፣ Hawassa Industrial Park- Flagship Park በቻይና ሲቪል ኢንጂነሪንግ ኮንስትራክሽን ኩባንያ የሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ በ240 ሚሊዩን ዶላር ወጪ ተገንብቶል፡፡ በመንግስት፣በአለም ባንክና በባህር ማዶ ሀገራት ገንዘብ ብድር የተሠራ ሲሆን በቻይና ካንፓኒ ሲሲኢሲሲ ኮንትራክተር የተገነባ በ2016 የተጠናቀቀ ነበር፡፡ ከጁቡቲ ወደብ 998 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በመገኘቱ ተጨማሪ የትራነስፖርት ውጪ ስላለው በዓለም አቀፍ ንግድ ላይ በርካሽ ሽጦ ተወዳዳሪ መሆን አይቻለውም፡፡ Location : Located approximately 275 kms south of Addis Ababa/Eco- Industrial Park with zero liquid discharge(ZLD) facility/ Cluster: Specialized in textile & garment/ Land area: 130 ha , Phase I (Shed & land lease status: 22 sheds of 11000 m2 /12 sheds of 5500 m2 /3 specialized sheds )1st phase: >30 ha factory buildings, business district, residential quarters etc /Fully occupied by international & domestic manufacturers
{5} የመቐለ ኢንዱስትሪ ፓርክ፣ Mekelle Industrial Park/ የቻይና ሲቪል ኢንጂነሪንግ ኮንስትራክሽን ኩባንያ የመቐለ ኢንዱስትሪ ፓርክ በ125 ሚሊዩን ዶላር ወጪ ለመገንባት ውል ፈርሞል፣በመንግስት፣በአለም ባንክ ብድር የተገነባ ሲሆን በቻይና ካንፓኒ ሲሲኢሲሲ ኮንትራክተር የተገነባ ሲሆን፣ ፡፡ ኩባንያው ከዚህ በፊት ከሚኤሶ ድሬዳዋድረስ ያለውን የባቡር መስመር በ1.2 ቢሊዩን ዶላር ወጪ ሠርቶል፡፡ ከጁቡቲ ወደብ 750 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በመገኘቱ ተጨማሪ የትራነስፖርት ውጪ ስላለው በዓለም አቀፍ ንግድ ላይ በርካሽ ሽጦ ተወዳዳሪ መሆን አይቻለውም፡፡ Proximity to Port of Djibouti: 750 km /Labor: 1 million people in & around city/ Cluster: Textile & Apparel and Food Processing/ Land area: 1000 ha/ 1st phase: 75 ha
{6} የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ፣ Kombolcha Industrial Park/የቻይና ሲቪል ኢንጂነሪንግ ኮንስትራክሽን ኩባንያ የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ በ125 ሚሊዩን ዶላር ወጪ ለመገንባት ውል ፈርሞል፡፡ በመንግስት፣በህንድ መንግስት ብድር የተሠራ ሲሆን በቻይና ካንፓኒ ሲሲሲሲ ኮንትራክተር የተገነባ ሲሆን ፣ከጁቡቲ ወደብ 480 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በመገኘቱ ተጨማሪ የትራነስፖርት ውጪ ስላለው በዓለም አቀፍ ንግድ ላይ በርካሽ ሽጦ ተወዳዳሪ መሆን አይቻለውም፡፡ Proximity to port of Djibouti: 480 km, 6 km away from Kombolcha dry port/ Labor: 1 million people in & around city / Cluster: Textile & Apparel and Food Processing/ Land area: 700 ha/ 1st phase: 75 ha
{7} የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ፣ Adama Industrial Park በመንግስት ገንዘብ የተሠራ ሲሆን በጨርቃ ጨርቅና ምግብ ዘርፍ በቻይና ካንፓኒ ኮንትራክተር የተገነባ ሲሆን ፣ከጁቡቲ ወደብ 678 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በመገኘቱ ተጨማሪ የትራነስፖርት ውጪ ስላለው በዓለም አቀፍ ንግድ ላይ በርካሽ ሽጦ ተወዳዳሪ መሆን አይቻለውም፡፡ Proximity to port of Djibouti: 678 km/ Labor: 1 million/ Cluster: Textile & Apparel, vehicles assembly and Food Processing Land area: 2000 ha/ 1st phase: 120 ha 250 ሚሊዮን ዶላር ከቻይና የተገኘ ሲሆን ግንባታው በሁናን ፕሮቪንስ ካንፓኒ እንደሚሰራ ታውቆል፡፡
{8} የድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ፣{5.1} Dire Dawa Industrial Park/ በመንግስት፣ ገንዘብ የተሠራ ሲሆን በቻይና ካንፓኒ ኮንትራክተር የተገነባ ሲሆን፣ከጁቡቲ ወደብ 380 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ Location: Located in the eastern Ethiopia approximately 262 km from Djibouti / Proximity to port of Djibouti: 380 km / Labor: 1 million people in & around the city / Cluster: Multiple sectors including heavy industries, Textile & Apparel, vehicles assembly and Food Processing,electronic, paper & allied products, chemicals / Land area: 3000 ha/ Shed & land lease status: Total sheds 15 / 5 sheds of 11,000 m2 / 6 sheds of 5500 m2 / 4 sheds of 3000 m2 / 1st phase: 150 ha
{9} የጂማ ኢንዱስትሪ ፓርክ፣ በ2016 እኤአ ሲጠናቀቅ፣ በመንግስት፣ ገንዘብ የተሠራ ሲሆን በቻይና ካንፓኒ ሲሲሲሲ ኮንትራክተር የተገነባ ሲሆን ፣ከጁቡቲ ወደብ 1200 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በመገኘቱ ተጨማሪ የትራነስፖርት ውጪ ስላለው በዓለም አቀፍ ንግድ ላይ በርካሽ ሽጦ ተወዳዳሪ መሆን አይቻለውም፡፡ ለጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ኢንዱስትሪዎች ልማት የፕሮጀክቱ ወጪ 1.5 ቢሊዮን ብር የቻይናው ሲሲሲሲ ኮንትራክተር፣ አማካሪ ኤምኤች ኢንጂነሪንግ ሦስት የኢንዱስትሪ ፓርኮች በ10.5 ቢሊዩን ብር ሊገነቡ ነው (ጥር 14 ቀን 2009ዓ/ም) የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በአዲስ አበባና ጂማ ከተሞች በ10.5 ቢሊዮን ብር ሊገነባ መሆኑን አስታወቀ፡፡ የጅማ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ዘጠኝ ትልልቅ ፋብሪካዎች ሼድ በ81 ሚሊዮን ብር የግንባታ ወጪ ተሠርቶል፣
{10} አረርቲ ኢንደስትሪያል ፓርክ Arerti Industrial Park/ በመንግስት፣ ገንዘብ የተሠራ የኮንስትራክሽንና የቤት ውስጥ እቃዎች ዘርፍ ሲሆን በቻይና ካንፓኒ ሲሲሲሲ ኮንትራክተር የተገነባ ሲሆን ፣ከጁቡቲ ወደብ 860 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በመገኘቱ ተጨማሪ የትራነስፖርት ውጪ ስላለው በዓለም አቀፍ ንግድ ላይ በርካሽ ሽጦ ተወዳዳሪ መሆን አይቻለውም፡፡ Proximity to Port: 50 km away from Mojo dry port/ Proximity to Railways: 50km away from Mojo Station of Addis Ababa to Djibouti Railway/ Proximity to Addis Ababa: 105 km / Cluster: Construction Materials & House hold appliance manufacturing/ Land Area: 100 ha
{11} ደብረብርሃን ኢንደስትሪ ዞን፤ Debre Berhan Industrial Park በመንግስት፣ ገንዘብ የሚሰራ ሲሆን በኮንትራክተር የተገነባ ሲሆን ፣ከጁቡቲ ወደብ 895 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በመገኘቱ ተጨማሪ የትራነስፖርት ውጪ ስላለው በዓለም አቀፍ ንግድ ላይ በርካሽ ሽጦ ተወዳዳሪ መሆን አይቻለውም፡፡ ከተማው በተከለሉ ሦስት ኢንደስትሪ ዞኖች ውስጥ ለመገንባት የቱርኩ ማይ ሹ በ1.2 ቢሊዩን ብር የጫማና ቆዳ ውጤቶች ፋብሪካ ለመገንባት፣ጁኒፕር ግላስ ኢንዱስትሪ በ900 ሚሊዩን ብር የጠርሙስ ፋብሪካ ግንባታ፣ቲጂቲ ትራክተር መገታጠሚያ በ59 ሚሊዩን ብር ፣ተገኔ ሙሉ ፐልፕና ወረቀት ፋብሪካ በ73.4 ሚሊዩን ብር፣ራህማ ኑርዬ ፒቪሲ ፋብሪካ በ42 ሚሊዩን ብር ፣ ሙሉነህ ጎሳዬ መድሃኒት ፋብሪካ በ69 ሚሊዩን ብር፣ ፒቲአይቲ ብረታ ብረት ፋብሪካ በ85.2 ሚሊዩን ብር የመሠረት ድንጋይ አስቀምጠዋል፡፡ የብአዴን፣የፓርቲ ኢንተርፕራይዝ ዳሽን ቢራ ፋብሪካ በከተማዋ ገንብቶል እንዲሁም ሐበሻ ቢራ ፍብሪካ፣የተለያዩ አልኮል መጠጦችና የጨርቃ ጨርቅ ፣የብረታ ብረትና የምግብ ኢንደስትሪዎች ኢንቨስትመንት በከተማዋ ይገኛሉ፡፡
{12} ሰንዳፋ ኢንደስትሪያል ዞን በቱርክ ባለሃብቶች ገነባል ተብሎ የሚጠበቅ ግዙፍ የኢንደስትሪ መንደር ይገኝበታል፡፡ የኢትዩ- ቱርክ የኢንደስትሪ ቀጠና አክጉን ግሩፕ የተባለው የቱርክ ኩባንያ በአስር ሚሊዩን ዶላር በሰንዳፋ አካባቢ ለመገንባት ላቀደው ኢትዩ-ተርኪሽ የኢንዱስትሪ ዞን 100 ሄክታር መሬት ተረክቦል፡፡ የወያኔ ዘመን የህወሓት የጦር አበጋዞች የኢኮኖሚ ፋሽን ከውሃ ማቆር ወደ ፋብሪካ ማቆር ተሸጋግሮል፡፡
{13} ሰበታ ኢንደስትሪያል ዞን ከአዲስ አበባ ከተማ በስተ ምዕራብ በኩል ረጲ በሚባለው አካባቢ ፋብሪካውን በ1948 እኤአ ተክሎ፣ቢያኔሎ ኢትዩጵያ ሊሚትድ በሚል መጠሪያ በግሪክ ተወላጆች የተቆቆመ ረጲ ሳሙና ፋብሪካ ነበር፡፡ ፋብሪካው ሮል እየተባለ የሚጠራውን ዲተርጀንት ሳሙና እያመረተ ለአውሮፓ ገበያ ያቀርብ የነበረ ነው፡፡ ረጲ ሳሙና ፋብሪካ በወታደራዊው መንግስት ዘመን በመንግስት ተወረሰ፡፡ በወያኔ ኢህአዲግ ዘመን፣ የመንግስት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ 5,280,000 ሚሊዩን ብር ለሊና ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ተሸጠ፡፡ የአልሳም ግሩፕ ኩባንያዎች አባል በሆነው ሊና ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በኩል በ1999 ዓ/ም ረጲ ሳሙና ፋብሪካን ከመንግስት በመግዛት ስያሜውን ወደ ረጲ ሳሙናና ዲተርጀንት አክሲዩን ማህበርነት በመቀየር ሲሰራ ቆየ፡፡ ፋብሪካው ለማስፋፍያ በተሰጠው 17,300 ካሬ ሜትር ላይ የ150 ሚሊዩን ብር ወጪ ግንባታ ማካሄዱና በ40 ሚሊዩን ብር ወጪ አዳዲስ ማሽነሪዎች መግዛቱን ኩባንያዉ ሃላፊ ገልጸዋል፡፡ በሰበታ ከተማ ዲማ ቀበሌ ውስጥ በ100 ሄክታር መሬት ላይ የአምራች ኢንደስትሪ ኮምፕሌክስ ስር 14 ፋብሪካዎችን በአንድ ኢንደስትሪ መንደር ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ ግንቦት 2 ቀን 2007 ዓ/ም በጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ተቀምጦል፡፡ በፋብሪካዎቹ የሱፍ፣ አኩሪ አተርና የፓልም ዘይት ማጣሪያዎች፣ የገበታ ቅቤ ማምረቻ፣ የላውንደሪ ሳሙና፣ ሲንቴቲክ የልብስ ሳሙና፣ የገላ ሳሙና፣ የፈሳሽ ሳሙና፣ የዱቄት ሳሙና፣ የባኞ ቤት ሳሙና ማምረቻ ፋብሪካዎችን ጨምሮ የማዳበሪያ፣ የስንዴ ዱቄት፣ የማካሮኒና የፓስታ እንዲሁም የሰሊጥ ማበጠሪያ ፋብሪካዎች በ7 ቢሊዩን ብር(በ350 ሚሊዩን ዶላር) ወጪ እንደሚገነቡ አስታውቀው ነበር፡፡ በረጲ-ዋልማር ሰበታ ኢንደስትሪያል ዞን 2000 ሰዎች የስራ እድል ይፈጥራል ተብሎ ይታመናል፡፡
{14} አይሻ ኢንደስትሪያል ዞን፣ (Aysha, Somali Regional State;) በመንግስት፣ ገንዘብ የሚሰራ ሲሆን ፣ከጁቡቲ ወደብ ኪ/ሜ ርቀት ላይ በመገኘቱ ተጨማሪ የትራነስፖርት ውጪ ስላለው በዓለም አቀፍ ንግድ ላይ በርካሽ ሽጦ ተወዳዳሪ መሆን አይቻለውም፡፡
{15} ባህር ዳር ኢንዱስትሪያል ፓርክ፣ በ2016 እኤአ ሲጠናቀቅ፣ በመንግስት፣ ገንዘብ የተሠራ ሲሆን በጨርቃ ጨርቅ ዘርፍ በኮንትራክተር የተገነባ ሲሆን ፣ከጁቡቲ ወደብ 985 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በመገኘቱ ተጨማሪ የትራነስፖርት ውጪ ስላለው በዓለም አቀፍ ንግድ ላይ በርካሽ ሽጦ ተወዳዳሪ መሆን አይቻለውም፡፡
{16} ምሥራቃዊ ኢንደስትሪያል ዞን/Eastern Industrial Zone (EIZ)) / የተለዩ የኢኮኖሚ ዞኖች/ (Special Economic Zones) የቻይና ንብረት የሆነው፣ ከጁቡቲ ወደብ 860 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በመገኘቱ ተጨማሪ የትራነስፖርት ውጪ ስላለው በዓለም አቀፍ ንግድ ላይ በርካሽ ሽጦ ተወዳዳሪ መሆን አይቻለውም፡፡ የተለዩ የኢኮኖሚ ዞኖች( Special Economic Zones) ምሥራቃዊ ኢንደስትሪያል ዞን (Eastern Industrial Zone (EIZ)) ወይም ኢንደስትሪያል ፓርክ በኢትዬጵያ ከአዲስአበባ ስሜን ምስራቅ 37 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው በዱከም ከተማ ተገንብቶ ይገኛል፡፡ በዱከም በ500 ሄክታር ላይ የተገነባው ምሥራቃዊ ኢንደስትሪያል ዞን በአይነቱ የተለየ የቻይና ኢንቨስትመንት አካል ነው፡፡ በ2007 እኤአ የንጋንግ ግሩፕና( Yonggang Group) ኪያኦን ግጉፕ( Qiyuan Group) የሆኑት በዛንግጃአጋንግ ከተማ የሚገኑት ሁለቱ የብረት ፋብሪካዎች በቻይና የንግድ ሚኒስትር የወጣውን ጫረታ በማሸነፍ ሥራ ጀመሩ፡፡ በኢትዬጵያ ይህ የተለየ የኢኮኖሚ ዞኖች ምስረታ የመጀመሪያውና ትልቁ ኢንደስትሪያል ፓርክ በሃገሪቱ ለመሆን በቅቶል፡፡ የኢትዬጵያ መንግስት ይህን ፕሮጀክት ከዘለቄታ የኢኮኖሚ እድገትና ከድህነት ቅነሳ ጋር በማዛመድ የኢንደስትሪያል ዘርፍን ለማሳደግ አቅዶል፡፡ ኢትዬጵያ መንግስት ኢንደስትሪ ሚኒስትር የኢኮኖሚ ዞኑ ውስጥ የጨርቃ ጨርቅና የልብስ፣የህንፃ መሣሪያዎች ዕቃ ማምረቻ፣የማኒፋክቸሪንግና የግብርና ምርት ማቀነባበሪያ አገልግሎት እንዲስፋፉ ይፈልጋሉ፡፡ በአሁኑ ግዜ 11 የቻይና ካንፓኒዎች በኢንደስትሪያል ፓርክ ለመስራት ፊርማቸውን አኑረዋል፡፡
ሁጃአን( Huajian) የቻይና የጫማ ፋብሪካ የባህር ማዶ ገበያ ኢንቨስተር በኢትዬጵያ ውስጥ 20 ሚሊዩን ጥንድ ጫማዎች በአመት ወይም ሁለት ሽህ ጥንድ ጫማዎች በቀን በማምረት ላይ ይገኛል፡፡ የጫማ ፋብሪካው በስመ ጥሩ ንግድ ምልክት ብራንድ ስም በማምረት በዓለም ዓቀፍ ንግድ በመሰማራት ለአሜሪካና አውሮፓ በማቅረብ ላይ ይገኛል፡፡ በአሁኑ ግዜ 1600 ሠራተኞች ያሉት ሲሆን አብዛኛዎቹ ኢትዬጵያዊ እንደሆኑ ይታወቃል፡፡ የሁጃአን ማኒፋክቸሪንግ በኢትዬጵያ ውስጥ ርካሽ የሠራተኛ ጉልበት ዋጋ፣ በርካሽ ዋጋ ሰፊ የቆዳ አቅርቦት አግኝቶል፡፡ ፋብሪካው ሰፊ የግንባታ ቦታ፣የተሞላ የኤሌትሪክና ውኃ አቅርቦት፣ የመንገድ መሰረተልማትና የታክስ እፎይታና ከውጭ ለሚገቡ እቃዎች/ማሽነሪዎች ወዘተ ከቀረጥ ነፃ ፖሊሲ በማግኘት ምርቶቹን ወደ አሜሪካና አውሮፓ ገበያ በማቅረብ ከፍተኛ ትርፍ አግኝተዋል፡፡ የሁጃአን የቻይና የጫማ ፋብሪካ ሁሉንም ምርቶች ለባህር ማዶ ገበያ በማቅረብ በ2011 እኤአ 250 ሚሊዬን ብር (12 ሚሊዩን ዶላር በአመት)ገቢ አግኝቶል፡፡ ‘’Huajian has a modest outfit in Dukem, about 40km south of Addis Ababa. It employs 1,600 Ethiopians, all high school graduates or above, and ships more than $1m worth of shoes each month to the US and the UK for Guess, Naturalize and Clarkes. ‘’
የቻይና ካንፓኒዎች በኢትዬጵያ የኢንቨስትመንት ክንውን ከሚያሰሞቸው ደካማ ጎኖች መካከል የሚከተሉት ይጠቀሳሉ፡፡ የምርት ሂደቱን ፍጥነትና ግዜ በምርትና ግዜ አንፃር እንደ ቻይና ማሳጠር አለመቻል፣የጉምሩክ የምርት የመላክ ሂደት ቀርፋፋነት፣የተማረ ሰው ኃይል ክህሎት ማነስና የአስተዳደር ልምድ እጦት እንዲሁም በአጠቃላይ የምርት መጎጎዣ አቅርቦት የትራንስፖርት ወጭ ከፍተኛ መሆን ፤የሰው ሃይል ወጭ፣የኪራይ ወጭ ከቻይና ሃገር ጋር ሲወዳደር ከፍተኛ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡በኢትዬጵያ የመሠረተ ልማት ኃላ ቀርነት የቢዝነስ/ የንግዱን ስርዓት አጠቃላይ ሁኔታ እንደጎዳው ይገልፃሉ፡፡ የመጀመሪያው በሃረሪቱ የኤሌትሪክ ኃይል መቆረጥ የኢንቨስተሩን ወጭ ጨምሮበታል፡፡ ሁለተኛው ከአዲስ አበባ እስከ ጂቡቲ ያለው አስፋልት አይሉት ኮሮኮንች መንገድ ትርንስፖርቱን ወደ ወደብ መድረሻ ግዜ በማርዘም ለተጨማሪ ወጭ መዳረጋቸውን ኢንቨስተሮች ይገልፃሉ፡፡ በሶስተኛ ደረጃ ደግሞ የቴሌኮምኒኬሽን ክፍያ ውድ መሆን ከቻይና ሃገር ካለው እናት ካንፓኒ ጋር የሚያደርጉትን ግንኙነት ተጨማሪ ወጭ እንደሆነባቸው ይገልፃሉ፡፡
‘’However, Huajian has faced considerable obstacles over the past 15 months. The cost of transportation to and from landlocked Ethiopia is just one of the problems. For every 12 containers shipped, eight containers are imported at a cost of $8,000 each, which adds an additional 6% to freight expenditure compared to Huajian’s Chinese operations. Of this, $4000 goes on transport from China to the port of Djibouti; the rest is swallowed up on the 700km journey to Addis Ababa.’’
ለማጠቃለያ የቻይና የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ፍሰት በኢትዮጵያ ለሰው ሃብት ልማት የሥራ ፈጠራ በማበርከትና ተጨማሪ ምርቶች ለኢትዬጵያ ኢኮኖሚ ማበርከት ችሎል፡፡ ወደፊት ኢትዬጵያ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ፍሰት ለመሳብ የጉምሩክ ዕቃ ማስገባትና ማስወጣት ደንቦንና የንግድ ስርአቶን ቀልጣፋ ማድረግ ይጠበቅባታል፡፡ የውጭ ምንዛሪ መለዋወጥ ሥራን ማመቻቸትና የውጭ ምንዛሪ ግብይይት በግልፅነት ፖሊሲ ማውጣት፡፡ የግብር አከፋፈልና አስተዳደር ስርዓትን በዘለቂታና በቀልጣፋ ሁኔታ ማሻሻል አንገብጋቢ ጉዳይ ሲሆን በተለይ በየግዜው የሚቀያየር ህግና ደንብ፤መመሪያና ፖሊሲ የባህር ማዶ ኢንቨስተሮችን አይስብም ይልሉ፡፡ እንዲሁም አንድ ወጥ የሰራተኛ ህግና ደንብ ማውጣት ምርታማነትን፣ብቃትንና ቅልጥፍናን በመጨመር ከፍተኛ ምርት በማምረት ብቃት ያለው ሰራተኛን መፍራት ይቻላል፡፡
‘’ Huajian signed a memorandum of understanding with the China-Africa Development Fund, a private equity fund that facilitates Chinese investment on the continent, to jointly invest $2bn over a decade in creating a light-manufacturing special economic zone in Ethiopia. The company has already leased 300ha of land in Lebu, on the outskirts of the Ethiopian capital, where it plans to build a shoe city, with accommodation for 200,000 people and factory space for other manufacturers of footwear, handbags, accessories and components. Ms Hai expects construction to begin there later this year. ‘’
http://www.bdlive.co.za/africa/africanbusiness/2013/04/04/ethiopia-could-be-shoemaker-to-the-world
‘’Abstract: China’s investment activities in Africa have attracted significant interest in academic, policy and media circles in the last decade. Adopting country case studies analysis, findings indicated that Chinese investment relations with Africa have its good, bad and ugly sides. On the good side, China has established special economic zones which have the potential to build economic linkages with the local economy. However, the linkages are mainly forward, involving logistics, forwarding, and insurance and financial services. Backward linkages are fostered to the extent that the Chinese firms contract out transportation and catering services for their employees and sub-contract with local firms. The bad side includes the limited employment quota for local citizens, poor labour standard, limited technology transfer, and the quality of Chinese construction. The ugly side includes tax evasion and support to dictatorial regimes in Africa. Chinese companies should be well controlled and the legislation that guides their business conduct should be fully enforced.’’ Asia Pacific and Globalization Review, Vol. 3, No. 1, 2013 © 2013 APGR https://journals.macewan.ca/index.php/apgr/index Asia Pacific and Globalization review (ISSN 1920-1206) Sino-Africa Investment Relations: The Good, The Bad and The Ugly: Musibau Adetunji Babatunde, Department of Economics, University of Ibadan,Ibadan, Oyo State,Nigeria:E-mail: [email protected]
የኤርትራ መከላከያ ሠራዊት ከጦርነት ቀጠናው ጦሩን አስወጥቶል፡፡ በመቐለ የመሸገው ፀረ-ዲሞክራሲ ኃይል የኢትዮጵያን መከላከያ ሠራዊት የአየር ኃይል፣ ታንከኛና፣ የጦር ግምጃ ቤት ወደ ነበረበት ሥፍራ እስካልተመለሰ ደረስ ነፃነት የለም፡፡ የወያኔ የጦር አበጋዞች መንግሥት ህገመንግሥቱን ባለማክበር ህገወጥ ወንጀለኞችንና ሙሰኞችን የትግራይ ህዝብ አሳልፎ ለፍርድ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ወያኔ በህገወጥ መንገድ የሚያዘዋውረው የመሣሪያና የገንዘብ ዝውውር የተጀመረውን የዲሞክራሲ ለውጥ ለማጨናገፍ በመሆኑ ህብረተሰቡ ነቅቶ መጠበቅ ይኖርበታል፡፡
ምንጭ
- Email: [email protected]
- Web: investethiopia.gov.et
- Industrial Parks Development Corporation Web: ipdc.gov.et
- Ministry of Industry Web: moin.gov.et