የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በኢትዮጵያ

https://gdb.voanews.com/12265523-e056-49db-8358-c2e7eea06096_tv_w800_h450.jpg

ኢትዮጵያ የውስጥ ችግሮቿን በራሷ የመፍታት አቅም እንዳላት እንደምታምን እና ለዚህም የበኩሏን ድጋፍ እንደምታደርግ ቻይና አስታወቀች።  

በኢትዮጵያ የሥራ ጉብኝት ያደረጉት የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ፣ ዜጎቻቸውን “ከኢትዮጵያ እንዲወጡ” በሚል በአንዳንድ ሃገሮች መንግሥት የሚተላለፉ መልዕክቶችን ሀገራቸው እንደምትቃወም መግለጻቸውን የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል፡፡  

ሚስተር ዋንግ ኢትዮጵያን የጎበኙት “በአስቸኳይ ከኢትዮጵያ ውጡ” በማለት ተደጋጋሚ ጥሪዎች በሚቀርቡበት ወቅት መሆኑን በትዊተር ገጻቸው የጠቆሙት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን፣ ይህንንም “ሰፊ ተቃርኖ” ሲሉ ገልጸውታል፡፡ በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት የተለያዩ የውጭ ኃይሎች ለተቀናቃቸው ድጋፍ ያደርጋሉ በሚል የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት በተደጋጋሚ ክስ ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡  

Source: Link to the Post

Leave a Reply