የቻይና ዶክተሮች በደቡብ ሱዳን ከ2 ሺ በላይ ለሚሆኑ ሰዎች ህክምና መስጠታቸው ተሰምቷል፡፡

በደቡብ ሱዳን ከ2 ሺ በላይ ሰዎች ህክምና ያገኙት በነፃ ስለመሆኑ ተነግሯል፡፡ከጁባ እስከ ቴሬኬካ ያለውና በደቡብ ሱዳን ረዥሙ የመንገድ ሥራ በርካቶችን በቀን ሠራተኛነት የሚያሰራ ሲሆን የመንገድ ሥራ ተቋራጩም የቻይናው ሻን ዶንግ ሃይ ሥፒድ ኩባንያ ነው፡፡

በደቡብ ሱዳን የቻይናው አምባሣደር ኑዋ ኒንግ በሰጡት ማብራሪያ ስምንተኛው የቻይና የህክምና ቡድን በዚያች ሀገር ላሉ ድሃ ማኅበረሰብ የነፃ ህክምና አገልግሎት ለመስጠት ሳያቅማማ መጥቷል ነው ያሉት፡፡እንደ አምባሣደሩ ማብራሪያ የነፃ ህክምናውን ካገኙት የደቡብ ሱዳን ዜጐች መካከል በዚያ የመንገድ ሥራ ፕሮጀክት ውስጥ የሚሰሩትም ተጠቃሚዎች ሆነዋል ሲል የዘገበው ቻይና ኦርግ ነው፡፡

ቀን 08/04/2013

Source: Link to the Post

Leave a Reply