የቼኒና የሃግማን ትንቅንቅ ትርጉም

https://gdb.voanews.com/01630000-0aff-0242-cd78-08da808b2584_tv_w800_h450.jpg

የዩናይትድ ስቴትስ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ጠንካራ ሪፐብሊካን ተቀናቃኝና የዋዮሚንግ ግዛትን ወክለው በተወካዮች ምክር ቤት አባልነት ያገለገሉት ሊዝ ቼኒ ፓርቲያቸው ለአጠቃላይ ምርጫ ዝግጅት ትናንት ባደረገው ቅድመ ምርጫ ተሸንፈዋል።

በአንፃሩ የትረምፕን ድጋፍ ያገኙት ተቀናቃኛቸው ኻሪየት ሃግማን አሸንፈዋል።

የቀድሞው የአሜሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት ዲክ ቼኒ ሴት ልጅ የሆኑት ሊዝ ቼኒ በሀግማን መሸነፍ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ደጋፊዎች ባለፈው ዓመት በኮንግረሱ ላይ ያደረጉትን ወረራ ተከትሎ በወንጀል እንዲጠየቁ ድጋፍ የሰጡ ሪፐብሊካኖችን ከሥልጣን ለማስወገድ ለሚያደርጉት ዘመቻ እንደ ትልቅ ድል ይቆጠራል ተብሏል።

አሸናፊዋ ሃግማን “ለፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ትልቅ ክብር እንዳላቸው” ሲናገሩ የተሸነፉትና በኮንግረሱ ላይ በተካሄደው ጥቃት ላይ ምርመራ እያካሄደ ያለውን ኮሚቴ በምክትል ሊቀመንበርነት እየመሩ ያሉት ቼኒ ሽንፈታቸውን ሲቀበሉ ባደረጉት ንግግር አጋጣሚው “የፖለቲካ ህይወታቸው አዲስ ምዕራፍ መክፈቻ መሆኑን”ና ትረምፕ ዳግመኛ ወደ ዋይት ሃውስ እንዳይደርሱ የሚያደርጉትን ትግል የሚያጠናክሩበት እንደሆነ አመልክተዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply