የችሎት ውሎ ጋዜጠኛ መዓዛ መሃመድና ጸሃፊ አሳዬ ደርቤ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበው የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ! ጥቅምት 15 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር ከሳምንት በፊት…

የችሎት ውሎ ጋዜጠኛ መዓዛ መሃመድና ጸሃፊ አሳዬ ደርቤ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበው የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ! ጥቅምት 15 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር ከሳምንት በፊት ከእስር የተፈቱት ጋዜጠኛ መዓዛ መሃመድና ጸሃፊ አሳዬ ደርቤ ዛሬ ጥቅምት 15/2015 ዓ.ም የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበው የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ የፈቀደላቸውን የዋስትና መብት ተክትሎ ጥቅምት 3/2015 ከእስር የወጡት እነ ጋዜጠኛ መዓዛ ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረቡት ዓቃቤ ህግ የመሰረተባቸው ክስ ላይ የተከሳሽ ጠበቆች የክስ መቃወምያ ካላቸው ለመስማትና የእምነት ክህደት ቃላቸውን ለመቀበል ነው፡፡ ነገር ግን ከእነ መዓዛ መሃመድ ጋር በአንድ መዝገብ የተከሰሰውና በእስር ላይ የሚገኘውን ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይን ፖሊስ ዛሬ ችሎት አላቀረበውም፡፡ ፍርድ ቤት የቀረቡት ተከሳሾች ሁለተኛ ተከሳሽ አሳዩ ደርቤ አቃቢ ህግ በመሰረተው ክስ ላይ የገለፀውን ቃለ መጠይቅ ማድረጋቸውን አምነው ሆኖም ግን ከአንድ ሰዓት በላይ ከተደረገ ቃለ መጠይቅ ላይ ሀሳቦች ተቀንጭበው ወጥተውና ከአውዳቸው ውጪ ተርጉመው የቀረቡ በመሆናቸው ጥፋተኛ አያስብለኝም ሲሉ የእምነት ክህደት ቃላቸውን የሰጡ ሲሆን ሶስተኛ ተከሳሽ ጋዜጠኛ መሀመድ በበኩላቸው ቃለ መጠይቁን ማድረጋቸውን አምነው ነገር ዜጎች ሀሳባቸውን በነፃነት የመግለፅ መብት አላቸው ሚዲያዎች ደሞ ለህዝብ ማድረስ የተመሰረቱበት አላማ ነው። ይሄን ማድረጌ ጥፋተኛ አያደርገኝም ሲሉ የእምነት ክህደት ቃላቸውን መስጠታቸውን ባልደረባችን ምስራቅ ተፈራ ከችሎት ዘግባለች። በተመሳሳይ ጋዜጠኛና የታሪክ ምሁሩ ታዲዎስ ታንቱ ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን በችሎቱ የተሰየመ ዳኛ ባለመኖሩ ለ ጥቅምት 25/2015 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል። ሮሃ ሚዲያ እንደዘገበው ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply