
#የችሎት ውሎ ፍ/ቤቱ ፖሊስ በጋዜጠኞቹ ላይ የጠቀቀውን ተጨማሪ 14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ፈቀደ! ግንቦት 04 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣ ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው እና ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ አስፋው ዛሬ ግንቦት 4 ቀን 2015 ዓ.ም ከረፋዱ 4:00 ላይ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት ቀርበው ነበር:: ጋዜጠኞቹ በሁከትና ብጥብጥ ተጠርጥረዋል በሚል ቀደም ሲል አራዳ ፍርድ ቤት ቀርበው በዋስ እንዲወጡ ተወስኖላቸው የነበረ ሲሆን የፌደራል ፖሊስ ውሳኔውን በመተው በሌላ “በሽብር” ጠርጥሬያቸዋለሁ በሚል ነው ወደልደታ ፍርድ ቤት ያዛወራቸው:: ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበው በጠበቆቻቸው በኩል ጥፋተኛ አለመሆናቸውንና ህጉ ከሚፈቅደው ውጭ ጋዜጠኞቹ በቅድመ እስር እየተጉላሉ መሆኑን ተከራክረዋል:: በዋስ ወተው ጉዳያቸውን በውጭ እንዲከራከሩም ጠይቀው ነበር:: ይሁንና ፍርድ ቤቱ መርማሪ ፖሊስ የጠየቀውን የ14 ቀን ቀጠሮ ፈቅዷል ሲል ጋዜጠኛ አራጋው ሲሳይ አጋርቷል። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post