የኅዳሴ ግድብ አንዱ ተርባይንን ሥራ መጀመርን በተመለከተ የተሰናዳ ዝግጅት

https://gdb.voanews.com/c4310000-0aff-0242-8d6c-08d9f5701bc7_tv_w800_h450.jpg

ኢትዮጵያ ለአውሮፓ የኤሌክትሪክ ኃይል የማቅረብ ፍላጎት እንዳላት ትናንት የካቲት 13/2012 ዓ.ም የኅዳሴ ግድብ ካሉት 13 ተርባይኖች አንዱን መርቀው ሥራ ያስጀመሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ።

አጠቃላይ ግንባታው ወደ መጠናቀቁ የተቃረበውና ውሃ የማቆሩን ሁለት ዙሮች በተሳካ ሁኔታ የጠናቀቀው የኅዳሴ ግድብ አንዱን ተርባይን ሥራ ያስጀመሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ግብጽ እና ሱዳን በግድቡ ላይ ያላቸውን አቋም በመቀየር ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር እንዲቆሙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ግብጽ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቷ በኩል ባወጣችው መግለጫ፣ ኢትዮጵያ ግድቡ ኃይል ማመንጨት መጀመሩን ተቃውማለች፡፡

ግብጽ ያሰማችውን ተቃውሞ ተንተርሶ የአሜሪካ ድምፅ ለትንታኔ የጋበዛቸው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲው የፖለቲካ ሳይንስና የዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህርና የዓለም አቀፍ የውሃ ጉዳዮች አዋቂው ዶ/ር ያዕቆብ አርሳኖ “በህዳሴ ግንባታም ሆነ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት በተከናወነው ሥራ የተጣሰ ምንም ዓይነት ሥምምነት የለም” ብለዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply