የነሃሴ 13 ቀን 2014 ዓ.ም የኢትዮ ማለዳ የዜና ሰዓታችን ከያዛቸው ጉዳዮች መካከል፦ በዛሬው የኢትዮ ማለዳ የዜና ሰዓታችን ( ከ12:30-2:30)-ከቤት ሳንወጣና ስፖርታዊ ጉዳዮችን ትሰማ…

የነሃሴ 13 ቀን 2014 ዓ.ም የኢትዮ ማለዳ የዜና ሰዓታችን ከያዛቸው ጉዳዮች መካከል፦

በዛሬው የኢትዮ ማለዳ የዜና ሰዓታችን ( ከ12:30-2:30)

-ከቤት ሳንወጣና ስፖርታዊ ጉዳዮችን ትሰማላችሁ

-በመንገዳችን ላይ መሰናዷችን ፦
ቡሄ ወይም ደብረ ታቦር በኢትዮጵያ የክረምት የመጨረሻው ወር ነሐሴ ውስጥ የሚከበር በዓል ነው።
ክብረ በዓሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከምታከብራቸው በዓላት አንዱ ነው።

‹‹ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት፤ ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት›› እየተባለ በታዳጊዎችና ሕፃናት በክብረ በዓሉ እለት ይነገራል፣ ለዓመታት የሚነገርም ሆናል።

አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ሕፃናት ቡሄን ሲያከብሩ አግኝተናቸው አነጋግረናቸዋል፤ትሰሙታላችሁ፡፡

ለጤናችን፡-

በዓለማችን ከ650 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ከመጠን በላይ በሆነ ዉፍረት ይሰቃያሉ፡፡
ከዚ ዉስጥ 39 በመቶ የሚሆኑት እድሜያቸዉ ከ18 ዓመት በታች ነዉ፡፡
በዛሬዉ የጤና መሰናዶ ከዚህ ዉፍረት መላቀቅ ስለቻሉ እና የተስተካከለ አቋም መገንባት የቻሉ ባለታሪክ ይዘናል፡፡

ፍተሻ፡-
የጉራጌ ዞን በክልል የመደራጀት ጥያቄ ባልተረጋጋው የሃገሪቱ ፖለቲካ ላይ ተጨማሪ ችግር እንዳይፈጥር ስጋት ፈጥሯል፡፡
የዘርፉ ባለሙያዎች ህገ መንግስቱ መርህ ሳያስቀምጥ፣ ዜጎች የጠየቁትን ጥያቄ ሊከለከሉ አይገባ ይላሉ፡፡
ጉዳዩን በፍተሻችን ተመልክተነዋል፡፡

ኢትዮ ገበያ፡-

ዳሽን ባንክ በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነውን አይ ቢኤም ክላውድ ፓክ የተሰኘ ቴክኖሎጂ ተግባራዊ አድርጓል፤
የሀገር ውስጥ አምራቾችን በአለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ ለማድረግ የሚያስችል ስምምነት ስለመደረጉም ሰምተናል–በኢትዮ ገበያችን እንመለከተዋለን፡፤

የዓለም ጉዳይ፡-
በሩሲያና ዩክሬን ጦርነት ምክንያት የአለማችን ግዙፉ የኒኩሊየር ጣቢያ አደጋ ላይ ይገኛል::
ዛፖርዢያ የተሰኘው ይህ የኒኩሊየር ጣቢያ ጥቃት የሚደርስበት ከሆነ አደገኛ ጨረሮች አፈትልከው ስለሚወጡ በዜጎች ላይ ትልቅ ስጋትን ደቅኗል
በጉዳዩ ላይ መፍትሄ ለመፈለግ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶንዮ ጉተሬዝና የተርኪዬው ፕሬዚዳንት ረሲጵ ጣይጵ ኤርዶሃን ወደ ዪክሬን አቅንተዋል
የአለም ጉዳያችን ትኩረቱን እዚህ ላይ አድርጓል

-እንዲሁም ሌሎች አዳድስ የሀገር ውስጥና ዓለምዓቀፋዊ ጉዳዮችንም አሰናድተንላችኋል።

የእለቱን ኢትዮ ማለዳ የሚያቀርብላችሁ መሳይ ገ/መድህን ነዉ ።
እንድታደምጡ ተጋብዛችኋል።

ለአስተያየትዎ ‘6321’ አጭር የጽሁፍ መልዕክት

Source: Link to the Post

Leave a Reply