የነሐሴ 11 ቀን 2014 ዓ.ም የኢትዮ ማለዳ የዜና ሰዓታችን ከያዛቸው ጉዳዮች መካከል፦ በዛሬው የኢትዮ ማለዳ የዜና ሰዓታችን ( ከ12:30-2:30)-ከቤት ሳንወጣና ስፖርታዊ ጉዳዮችን ትሰማ…

የነሐሴ 11 ቀን 2014 ዓ.ም የኢትዮ ማለዳ የዜና ሰዓታችን ከያዛቸው ጉዳዮች መካከል፦

በዛሬው የኢትዮ ማለዳ የዜና ሰዓታችን ( ከ12:30-2:30)

-ከቤት ሳንወጣና ስፖርታዊ ጉዳዮችን ትሰማላችሁ

-በመንገዳችን ላይ መሰናዷችን ፦

የእግረኛን መንገድ የሚዘጉ የግንባታ ግብአቶች ሰዎችን ለትራፊክ አደጋ እያጋለጡ ነው ተባለ።

በግንባታ ላይ ያሉ አንዳንድ ህንፃዎች ምንም መከላከያ ስለሌላቸው ከህንፃዎቹ ላይ የሚወድቁ ነገሮች እግረኛን እና ተሽከርካሪን ለጉዳት እንደሚዳረጉ መሆኑም ተነግሯል።
በዚህ ዙሪያ የተዘጋጀ ጥንቅር አለን።

-ለጤናችን፦

በአለም ላይ 50 ሚልዮን ሰዎች ከሚጥል ህመም ጋር ይኖራሉ፣80 በመቶ የሚሆኑት የሚኖሩት ደግሞ ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት ውስጥ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ሀገራችን ኢትዮጵያም ትገኝበታለች።

ለጤናችን ዛሬ ትኩረቱን ያደረገው በዚህ ህመም ነው።

-በፍተሻ ሰዓታችን፦

የአልሻባብ ጥቃት ኢትዮጵያን የመክበብ የእነ ግብፅ ዕቅድ ነው ተባለ።

በቅርቡ አልሻባብ በሶማሌ ክልል ያደረገው የማጥቃት ሙከራ ብቻውን ሳይሆን ከኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር እንደሆነም ተነስቷል።

የኢትዮጵያ መንግስትም አልሻባብን የማጥራት ሥራው ተጠናክሮ ቀጥሏል ብሏል።

በፍተሻችን ተመልክተነዋል።

በኢትዮ ገበያችን፦

በአነስተኛ በጀት የራሷን ስራ ጀምራ ህይወቷን በከፍተኛ ደረጃ ያሻሻለችን አንዲት ወጣት ተሞክሮ እናቀርብላችኋለን።

-በዓለም ጉዳይ፦

ኬንያ ከሰሞኑ ባካሄደችዉ ምርጫ ማግስት ስጋት እና ተስፋ አይሎባታል።

ተፎካካሪዎቹን ከለየዉ የምርጫ ኮሚሽኑ የቆጠራ ዉጤት ይፋ ካደረገ ጀምሮ መለስተኛም ቢሆኑ ተቃዉሞ እያቆጠቆጠ ይገኛል።

ትናንት ኦዲንጋም የሰጡት አስተያየት ከዚህ ቀደም የሃገሪቱን የምርጫ ታሪክ በጨረፍታ ለሚያዉቀው ስጋቱን ይረዳዋል።

የአለም ጉዳያችን የኬንያን የምርጫ ሁኔታ ከዚህ ቀደም ከተካሄዱት ምርጫዎች እና መዘዛቸዉን ጋር ያስቃኘናል።

-እንዲሁም ሌሎች አዳድስ የሀገር ውስጥና ዓለምዓቀፋዊ ጉዳዮችንም አሰናድተንላችኋል።

የእለቱን ኢትዮ ማለዳን የምታቀርብላችሁ የውልሰው ገዝሙ ናት ።

እንድታደምጡ ተጋብዛችኋል።

ለአስተያየትዎ ‘6321’ አጭር የጽሁፍ መልዕክት

Source: Link to the Post

Leave a Reply