
በምዕራብ ኦሮሚያ የምሥራቅ ወለጋ ዞን ዋና ከተማ የሆነችው የነቀምቴ ከተማ የገዢው የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ ባለሥልጣን ባልታወቁ ታጣቂዎች ተገደሉ። የነቀምቴ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ደሳለኝ ቦኮንጃ በታጣቂዎች በተፈጸመባቸው ጥቃት የተገደሉት ዛሬ ሐሙስ መጋቢት 21/2015 ዓ.ም. ነው። ግድያውን በተመለከተ የከተማ አስተዳዳሩ “ለሥራ ከቤታቸው ሲወጡ ባልታወቁ ሰዎች ተገደሉ” በማለት በፌስቡክ ገጹ ላይ የሐዘን መግለጫ አውጥቷል።
Source: Link to the Post